Friday, October 9, 2020 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation እነ ወ/ሮ አያልነሽ ፈንቴ እና ወ/ሮ ብርሃኔ ተካ የሰ-መ-ቁ182110 አመልካች ለዚህ ችሎት ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ/ም ባቀረቡት አቤቱታ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 62378 መጋቢት 11 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችሎት ማስረጃ ሳይሰማ አመልካች የሟች ሚስት አይደሉም በማለት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍርድ ቤቱም በመዝገብ ቁጥር 194677 መጋቢት 11 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችሎት ያቀረቡትን አቤቱታ በመሰረዙ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅሬታ አቅርበው ችሎቱም በመዝገብ ቁጥር 148513 የሰበር አቤቱታቸውን የሰረዘው ሆኖ እያለ እና የአሁን ተጠሪ በሰበር መዝገብ ቁጥር 152523 ባቀረቡት ቅሬታ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፊት የተሰጠን ውሳኔን ጠቅሶ ግራ ቀኙ የሟች ሚስቶች አይደሉም በማለት የሰጠውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ በመሻር በማስረጃ ተጣሪቶ እንዲወሰን ወደ ሥር ፍርድ ቤት መልሶት እያለ ፤ ይህ ውሳኔ ለአመልካችም ተፈፃሚነት ሊኖረው ሲገባ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ስላላቀረብሽ ውሳኔውን እንደተቀበልሽ ይቆጠራል በማለት ከክርክሩ እንዲወጡ በማድረግ ተጠሪ ብቻ ሚስትነታቸውን እንዲያረጋግጡ መደረጉ የእኩልነት መርህን የሚጥስ ነው በማለት ብይኑ ተሽሮ ሚስት መሆናቸውን በማስረጃ ማረጋገጥ እንዲችሉ እንዲወሰንላቸው ጠይቋል።…………. Previous Article አቶ ደጋረገ ሙሉ እና ወ-ሮ ውብናት ላቀ የሰ-መ-ቁ 181649 Next Article አግሪኮም ኢንተርናሽናል ኩባንያ ከ የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን Print 14725 Documents to download እነ ወ-ሮ አያልነሽ ፈንቴ እና ወ-ሮ ብርሃኔ ተካ የሰ-መ-ቁ182110(.pdf, 512.62 KB) - 1191 download(s)