Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation እነ ወ/ሮ ጌጤ ሙለታ(3ሰዎች) እና ወ/ሮ ብርሃኔ ካባ የሰ/መ/ቁ 249367 ለዚህ የሰበር አቤቱታ መቅረብ ምክንያት የሆነዉ ጉዳይ የዉርስ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ የተጀመረዉ በአምቦ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን በወረዳዉ ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካቾች በአምቦ ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ሟች አባታቸዉን ሙለታ ካባን ተክተዉ ከሟች አያቶቻቸዉ አቶ ካባ ዳባ እና ወ/ሮ ብርቱካን ፈካንሳ በዉርስ ሊያገኟቸዉ የሚገቡ በአምቦ ወረዳ ኢላሙ ጎርሚቲ ቀ/ገ/ማኅበር ዉስጥ በስድስት በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙትን የገጠር እርሻ ይዞታዎችን፣ በይዞታዎቹ ላይ የተፈሩ ቋሚ ሀብቶችንና የተለያዩ ከብቶችን ተጠሪ ከድርሻቸዉ በላይ ይዘዉ የሚገኙ መሆናቸዉን ገልፀዉ የዉርስ ሀብቶቹ ተጣርተዉ የሟች አባታቸዉን የዉርስ ድርሻ እንዲሁም ከፊሎቹ ከሳሾች ራሳቸዉን ችለዉ በጥገኝነት ሊያገኙ የሚገባቸዉን የዉርስ ድርሻ እንዲያገኙ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት በመጠየቅ ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ….. Print 2810 Documents to download 249367(.pdf, 828.74 KB) - 360 download(s)