Monday, February 8, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation እነ ወ-ሮ መሰረት ገብሬ እና ወ-ሮ ወርቋሃ ገብሬ የሰ-መ-ቁ 182459 የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 123889 በቀን 15/12/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 222328 በቀን 15/09/2011 ዓ.ም ያሳለፈው ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው። ለውሳኔው ምክንያት የሆነው ክርክር በስር የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተጀመረው የአሁን ተጠሪዎች ባቀረቡት የመቃወሚያ አቤቱታ ሲሆን የአሁን አመልካች የመቃወም ተጠሪ ነበሩ፡፡ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው ተጠሪዎች በቀን 08/12/2009 ዓ.ም ባቀረቡት የመቃወም አቤቱታ የአሁን አመልካች የአቶ ገብሬ ደስታ ልጅ ሳትሆን ልጅ ነኝ በማለት አመልክታ ፍ/ቤቱ ልጅ ነሽ በማለት የሰጠው ውሳኔ እንዲሰረዝልን በማለት ጠይቀዋል፡፡አመልካች በሰጡት መልስ በጋብቻ ውስጥ ስለተወለድኩ እና በህጉ ላይ የተመለከተውን የህግ ግምት ስላላስተባበሉ፤ ሟች እናትና አባቴ በ1965 ተጋብተው በ1969 ዓ.ም የተወለድኩ በመሆኑ፤ እንዲሁም ሟች አባቴ ልጅ መሆኔን አምኖ እንደ ልጅ ሲያስተምረኝ እና ሲንከባከበኝ ስለነበር አቤቱታቸው ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የመቃወም ተከሳሽ የሟች አቶ ገብሬ ደስታ ልጅ ናቸው በማለት የተሰጠው ውሳኔ ሊሰረዝ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ክርክርና ማስረጃውን መርምሮ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በሰጠው ውሳኔ አቶ ገብሬ ደስታ እና ወ/ሮ ዳዊ ገመቹ ጋብቻ መስርተው የነበረ መሆኑና የመቃወም ተከሳሽን ያሳደጓቸው መሆኑ በግራ ቀኙ የታመኑ ፍሬ ነገሮች ናቸው፡፡ የመቃወም ተከሳሽ አቶ ገብሬ ደስታ እና ወ/ሮ ዳዊ ገመቹ በ1965 ዓ.ም ተጋብተው በ1969 ዓ.ም ተወለድኩ በማለት ቢከራከሩም ምስክሮቻቸው ግን አቶ ገብሬ ደስታ እና ወ/ሮ ዳዊ ገመቹ መቼ እንደተጋቡ አላስረዱም፡፡ በተጨማሪም የመቃወም ተከሳሽ የልደት ምስክር ወረቀት ቢያወጡም የመቃወም ከሳሾች ምስክሮች በተመሳሳይ ቃል የመቃወም ተከሳሽ እናትና አቶ ገብሬ ደስታ ከመጋባታቸው በፊት የመቃወም ተከሳሽ ተወልደው የመጡ መሆኑን መስክረዋል፡፡ ሟች የመቃወም ተከሳሽን ያሳደጓቸው፣ ያስተማሯቸው እና በስማቸው የሚጠሩ መሆኑ በመቃወም ተከሳሽ ማስረጃዎች ቢረጋገጥም ይህን ያደረጉት ግን የሚስታቸው ልጅ በመሆናቸው ምክንያት እንጂ ልጃቸው በመሆናቸው አይደለም፡፡ በመቃወም ከሳሾች እና ተከሳሽ መካከል ዝምድና እንደሌለም በምርመራ ተጣርቷል፡፡ በመሆኑም የመቃወም ተከሳሽ የሟች አቶ ገብሬ ደስታ ልጅ ናቸው በማለት በቀን 09/10/2009 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 360(2) መሰረት ተሰርዟል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡…. Previous Article አቶ ብርሃኑ ታደሰ እና የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ቤቶች አስተዳደር ፅ-ቤት የሠ-መ-ቁጥር 190440 Next Article እነ መቶ አለቃ ኩምሳ ጨመዳ፣ወ-ሮ ኡርጌ መርጋ እና አቶ ካሳሁን አድነው የሰ-መ-ቁ 188071 Print 14212 Documents to download እነ ወ-ሮ መሰረት ገብሬ እና ወ-ሮ ወርቋሃ ገብሬ የሰ-መ-ቁ 182459(.pdf, 507.43 KB) - 969 download(s)