Thursday, October 7, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation እነ ወ-ሮ ሰሚራ ጀማል እና አቶ ናስር ሐጎስ የሠ-መ-ቁጥር 188406 ጉዳዩ ዳኝነት ሳይከፈል መዝገብ በነጻ ስለማስከፈት የሚመለከት ሆኖ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች አቤቱታዉን በማቅረብ የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት አቤቱታ እየተከራከሩበት ካለው ንብረት ውጭ ሌላ እንደሌላቸውና በጋብቻ ወቅት የተፈራው ንብረትም በፍርድ ስለታገደ መጠቀም እንደማይችሉ በመግለፅ በተጠሪ ላይ ለሚመሰርቱት የ32‚750‚000.00 ብር ክስ ለዳኝኘት የሚከፍሉት ገንዘብ እንደሌላቸዉ በመግለጽ መዝገቡ በነጻ እንዲከፈትላቸው የጠየቁ ሲሆን ተጠሪ በሰጡት መልስ አመልካች በጋብቻ ላይ እያሉ የሰሩት በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቤት ቁጥር 297 የሆነ መኖሪያ ቤት ፣ በመቐለ ከተማ መኖሪያ ቤት እንዲሁም በፒስ ደልውን ቴክኖሎጂ ሲስተም ሶልሽን ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ውስጥ አክሲዮን ያላቸው ስለሆነ ድሃ ስላልሆኑ የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍሉ መዝገብ ሊከፈትላቸዉ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡……. Previous Article እነ አቶ ኪሮስ መኮንን፣አቶ ዳዊት አማረ እና አቶ ኪሮስ ዳኘው የሰ-መ-ቁ- 188807 Next Article እነ ወ-ሮ የሺወርቅ ፈንታዉ እና ወ-ሮ ፀሀይነሽ ፈንታዉ የሠ-መ-ቁጥር 190450 Print 15865 Documents to download እነ ወ-ሮ ሰሚራ ጀማል እና አቶ ናስር ሐጎስ የሠ-መ-ቁጥር 188406(.pdf, 729.9 KB) - 1111 download(s)