/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

እነ ወ-ሮ ባህጃ ሳላህ፣ወ-ሮ ፎዚያ መሀመድ እና ወ-ሪት ምስራ አግዛ የሰ-መ-ቁጥር 184798

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካቾች ጥቅምት 14 ቀን 2012 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 84261 ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ እና የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 239167 ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታቸውን በማቅረባቸው ነው፡፡ ቅሬታቸውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካቾች የሚቃወሙባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የሚሉትን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ በስር ፍ/ቤት ያቀረብነው ክስ ተከሳሽ የአሁን ተጠሪ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ የእናቷን ውክልና መሰረት በማድረግ ውርስ እንዲጣራ አድርጋ ያከራከረንን ቤት ወደ እናቷ ስም ያዛወረች በመሆኑ ይሰረዝልን የሚል ሆኖ እያለ በውርስ ህግ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1000(1) መሰረት ክሳችንን በይርጋ ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን የሚል ነው፡፡………..

Previous Article አቶ አሰፋ በላይ፣ የጅማ ከተማ ወረዳ 1 ፖሊስ ጽ/ቤት ዋና ሳጅን ወጋየሁ አሊ እና የጅማ ከተማ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሰ-መ-ቁ 183680
Next Article እነ ሻለቃ ሰብሪ ቶፊቅ መሐመድ እና ሌ/ኮ/ል አለሙ ጌትነት አባተ የሰ-መ-ቁ 183941
Print
14800