Tuesday, March 9, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation እነ ወ-ሮ ብርሃን ገ/መድህን እና የሐውዜን ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሰ-መ-ቁ 182677 ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የይዞታ ክርክርን የተመለከተ ሲሆን አመልካቾች የሟች ቄስ ገ/መድህን ገብሩ ልጆች የአባታችን ስፋቱ 500 ካ.ሜ የሆነ የከተማ ነባር ይዞታ ቤትና ቦታ በስማችን ተመዝግቦ ማስረጃ እንዲሰጠን ይወሰንልን በማለት ያቀረቡትን ክስ መነሻ ያደረገ ሲሆን አመልካቾች በስር በሓውዜን ወረደ ፍርድ ቤት ከሳሾች የነበሩ ሲሆን ተጠሪ ተከሳሽ ነበር፡፡አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስም በሓውዜን ከተማ 03 ቀበሌ የሚገኝ አዋሰኙ በክሱ የተጠቀሰውን የሟች አባታችን ቄስ ገ/መድህን ገብሩ ነባር ይዞታና ቤት፣ አትክልትና ቦታ በአጣሪ ኮሚቴ የተጣራልን የሓውዜን ከተማ አስተዳደር ወደ ሓውዜን ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሊያስተላልፉልን ስላልቻሉ ክስ መስርተን የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ወደ ሓውዜን ከተማ ልማት /ማዘጋጃ ቤት/ ወስኖ በአፈፃፀም ከተላለፈልን በኋላ የሓውዜን ከተማ ማዘጋጃ ቤትን በመመሪያ መሰረት 500 ካ.ሜ ቦታ ይተላለፍልን ብለን ስንጠይቀው የሚሰጣችሁ 140 ካ.ሜ ቦታ ነው ስላለን ወደ አቤቱታ ሰሚ አካል ሄደንም ጉዳዪን ማየት የሚችለው ፍ/ቤት ነው የሚል መልስ ስለተሰጠን ሟች አባታችን ነባር ይዞታ የነበረው መሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ በደንብ ቁጥር 12/102/84 ክፍል 1-2 ለ-7 መሰረት 500 ካ.ሜ እንዲሰጠን ይወሰንልን በማለት አመልክተዋል፡፡ ተጠሪ በሰጠው መልስም የአሁን አመልካቾች 1ኛ አመልካች በተወሰነላቸው መሰረት እናስተላልፍላችሁ ብንላቸውም ፍቃደኛ አይደሉም፤ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች የሚመለከተቸው ከሆነ መጠያቅ የሚገባቸው 1ኛ አመልካችን እንጂ እኛን አይደለም፤ አመልካቾች የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰጠው ፍርድ መሰረት 140 ካ.ሜ እናስተላልፍላችሁ ብንልም 500 ካ.ሜ ካልሆነ አንቀበልም ብለዋል ስለሆነም የአመልካቾች ክስ አግባብነት ስለሌለው ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡…………. Previous Article አቶ ሀበን ግዑሽ እና ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ የሰ-መ-ቁ. 188331 Next Article አቶ ደጉ ናኔቻ እና የጉምሩክ ኮሚሽን የሰ-መ-ቁ 187878 Print 13558 Documents to download እነ ወ-ሮ ብርሃን ገ-መድህን እና የሐውዜን ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሰ-መ-ቁ 182677(.pdf, 529.02 KB) - 894 download(s)