እነ ዳዊት መንገሻ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መ.ቁ.209733
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የእምነት ማጉደል ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩም የተጀመረው የአሁን ተጠሪ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 675(1) ድንጋጌን ጠቅሶ በአሁን አመልካቾች ላይ በባሌ ዞን ጋሰራ ወረዳ ፍርድ ቤት ባቀረበው የወንጀል ክስ ነው፡፡ የክሱም ይዘት አመልካቾች የማይገባቸውን ብልፅግና ለራሳቸው ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስበው በወንጀል ተጠርጥሮ በክፍሉ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው በአጠቃላይ 656 ቁምጣ የዳንጎቴ ሲሚንቶ በወቅቱ በወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ንብረቱን ለማስቀመጥ የሚያስችል ቦታ ባለመኖሩ በአሁን አመልካቾች መጋዘን እንዲራገፍ ተጠይቀው ፈቃደኛ በመሆናቸው ንብረቱ በህገ ሲፈለግ ለማቅረብ ተስማምተው 1ኛ አመልካች 310 ቁምጣ፤ 2ኛ አመልካች ደግሞ 346 ቁምጣ ሲሚንቶ ከወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት ሰራተኛ ፈርመው በአደራ ከተቀበሉ በኋላ ሲሚንቶውን እንዲያቀርቡ ሲጠየቁ ለማቅረብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ነው፡፡……….
66
Documents to download
-
209733(.pdf, 1.01 MB) - 28 download(s)