Monday, July 18, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ኦርጋኒክ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ኦሮሚያ ብድር እና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር ሰ/መ/ቁጥር 217051. ክርክሩ በብድር የተሰጠ ገንዘብ አመላለስን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ግንቦት 9 ቀን 2013 ዓ.ም በአጭር ስነ ስርዓት ባቀረበው ክስ በግራ ቀኙ መካከል መስከረም 9 ቀን 2011 ዓ.ም በተደረገ የብድር ውል አመልካች ከ13% ወለድ ጋር ለመክፈል ተስማምቶ ብር 500,000 የተበደረ ቢሆንም ብድሩን ሳይከፍል 32 ወራት ስለቆየ ዋናውን ገንዘብ ብር 500,000፣ ወለድ ብር 188,980.36፣ በውሉ መሰረት ብድሩን ባለመክፈሉ በየቀኑ የሚታሰብ 0.25% መቀጮ ብር 450,000 በድምሩ ብር 1,138,890.36 እንዲከፍል ይወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ………. Print 16514 Documents to download 217051(.pdf, 830.17 KB) - 1524 download(s)