ኦቶሪኖ ከአንገት በላይ ሕክምና ማዕከል ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ነርስ ሚካኤል ዳንኤል የሰ/መ/ቁ 206729
ጉዳዩ የስራ ዉል መቋረጥ አግባብነት የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን የአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረበው ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከሐምሌ 16 ቀን 2010ዓ.ም ጀምሮ በፕሮፌሽናል ነርስ የስራ መደብ በወር ብር 11,200 ደመወዝ እየሰራሁ እያለ የዲስፕሊን ጥፋት ፈጽመሃል በማለት በ08/01/2013 ዓ.ም በህገ ወጥ መንገድ ከስራ አሰናበተኝ በማለት ስንብቱ ህገወጥ ነዉ ተብሎ የህገወጥ ስንብት ክፍያዎች እንዲከፈለው ዳኝነት የጠየቀ ሲሆን አመልካች በበኩሉ ባቀረበው መልስ ተጠሪ በቀን 08/01/2013ዓ.ም በነበረው ስብሰባ ላይ ሁከትና አምባጓሮ በመፍጠርና ለድብድብ በመጋበዝ በስራ ቦታ ረብሻና ሁከት በማድረጉ በአዋጅ ቁ/1156/2011 አንቀጽ 27(1)ረ መሰረት ያለማስጠንቀቂያ የሚያሰናብት የስነምግባር ጉድለት መፈጸሙን፤በኦፕራሲዮን ክፍል ውስጥ ዋና ሀኪም የሚናገረውን ንግግር በሹፈት በመድገም የታካሚ ስነልቦና እንዲታወክ ያደረገ በመሆኑ ባህሪውን እንዲያስተካክል በቅርብ አለቃው በቀን 30/07/2020 የቃል ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ቢሆንም ነሐሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ንግግሩን በመድገም የታካሚ ስነልቦና የሚጎዳ ንግግር በመናገሩ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ በፈፀመዉ ጥፋት ያለማስጠንቀቂያ የተሰናበተ መሆኑን፤የዓመት እረፍት እና ያልተከፈለ ደመወዝ እንዲወስድ ቢጠየቅም ፈቃደኛ ስላልሆነ የሚከፈል ክፍያ ባለመኖሩ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ በማለት መከራከሩን መዝገቡ ያሣያል፡፡………….
56
Documents to download
-
206729(.pdf, 859.7 KB) - 15 download(s)