/ Categories: CASSATION, Judgement, Cassation

ኦዲት ሰርቪስ ኮርፖሬሽን እና ፀጋ ረታ አስመጪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የሰ/መ/ቁ፡-197008

አመልካች የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ባቀረበው ክስ አመልካች የኮምፒዩተር እቃዎችን ለመግዛት ባወጣው ጨረታ ተጠሪ አሸንፎ እቃዎቹን አቅርቦ ክፍያ የተቀበለ ቢሆንም እቃዎቹን ከሰርቨሩ ጋር የሚያገናኙ ኬብሎችን ባለማቅረቡ ምክንያት እቃዎቹ የተፈለገውን አገልግሎት መስጠት አልቻሉም፡፡ በመሆኑም ኬብሎቹን እንዲያቀርብ ወይም በወቅቱ የገበያ ዋጋ የእቃዎቹን ግምት ብር 182,900 ወጪና ኪሳራን ጨምሮ እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ተጠሪ የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች እቃዎቹ ጉድለት ያለባቸው መሆኑን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በ1 አመት ውስጥ ክስ ስላላቀረበ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል፡፡…………

Previous Article የሟች ወ/ሮ ዋጋዬ ወ/ማርያም እና ወ/ሮ የሺሐረግ ከበደ የሰበር መ.ቁ 217691
Next Article አቶ ሰይድ እንድሪስ እና የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ፡- 205889
Print
13754

Documents to download