Tuesday, February 22, 2022 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation ኦዲት ሰርቪስ ኮርፖሬሽን እና ፀጋ ረታ አስመጪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የሰ/መ/ቁ፡-197008 ክርክሩ የሽያጭ ውልን መነሻ ያደረገ ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካች የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ባቀረበው ክስ አመልካች የኮምፒዩተር እቃዎችን ለመግዛት ባወጣው ጨረታ ተጠሪ አሸንፎ እቃዎቹን አቅርቦ ክፍያ የተቀበለ ቢሆንም እቃዎቹን ከሰርቨሩ ጋር የሚያገናኙ ኬብሎችን ባለማቅረቡ ምክንያት እቃዎቹ የተፈለገውን አገልግሎት መስጠት አልቻሉም፡፡በመሆኑም ኬብሎቹን እንዲያቀርብ ወይም በወቅቱ የገበያ ዋጋ የእቃዎቹን ግምት ብር 182,900 ወጪና ኪሳራን ጨምሮ እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ተጠሪ የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች እቃዎቹ ጉድለት ያለባቸው መሆኑን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በ1 አመት ውስጥ ክስ ስላላቀረበ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል እንደሚከተለው ቀርቧል………… Previous Article ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር እና እነ አቶ ታምሩ ደብሩ ሰ/መ/ቁ፡-191430 Next Article በደሴ ከተማ የሆጤ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና የወ/ሮ ማሚቴ ሁሴን ወራሾች እነ አያል አብርሃ የሰ/መ/ቁ፡-204074 Print 15812 Documents to download 197008(.pdf, 1007.51 KB) - 1202 download(s)