Thursday, March 27, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ከሊፋ አብዱራህማን እና ፍትሕ ሚኒስቴር ጥቅምት 05 ቀን 2017ዓ/ም የሠ/መ/ቁጥር 247066 የክስ ይዘት፡- አመልካች ከሌሎች ተከሳሾች ጋር በመሆን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1/ሀ)፣ 35፣38 እና የፀረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 3/3 ላይ የተደነገገዉን በመተላለፍ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) ሸኔን የፖለቲካ ወይም የርዕዮተ አለም ዓላማቸውን ለማራመድ በማሰብ ሕዝብን ወይም የተወሰነ የኅብረተሰብ ክፍል ለማሸበር ወይም መንግስትን ለማስገደድ በማሰብ የወንጀሉ ድርጊት በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን እና ውጤቱን የራሳቸው በማድረግ ወንጀሉን በቀጥታ በመፈጸምና ቀድመው ስምምነት በማድረግ በደምቢዶሎ ዩንቨርስቲ ውስጥ የተፈጠረውን የተማሪዎች ግጭት በመፍራት ወደ ቤተሰቦቻቸው የሚመለሱ የአማራ ክልል ተማሪዎችን ማገት አለብን በሚል ከቀን 22/03/2012ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የቄለም ወለጋ ዞን ሰዬ ወረዳ ማጣ ቀበሌ ላይ ገመዳ ረጋሳ፣13ኛ ተከሳሽ ጌታቸው ዮናስ፣ግርማ ይገዙ፣አህመዲን ኢተፋ፣ሞሴ ደጉማ፣ኢብሳ በቀለ፣ጃል ኡርጅ፣ጃል ጉቱ፣ኬኔሳ ዮናስ፣14ኛ ተከሳሽ ኦብሳ ፉፋ እና ሌሌች የኦነግ አባላትና አመራሮች ተሰብስበው ከተወያዩ እና ከተስማሙ በኋላ፡-1ኛ) በቀን 24/03/2012ዓ.ም በግምት ከቀኑ 7፡00 እስከ 8፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ሰዬ ወረዳ ሜንኮ ቀበሌ ቧንቧ ከተባለው ቦታ አካባቢ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዩንቨርስቲው ውስጥ የተፈጠረውን ግጭት በመፍራት ከደምቢዶሎ ከተማ ወረዳ መቻራ ከተማ 16ኛ ተከሳሽ ርስቁ አብደላ በሚያሽከረክረው ኮድ 3-34629 ኦሮ በሆነ ቀይ ዶልፊን ተሳፍረው ወደ ቤተሰቦቻቸው በመሄድ ላይ የነበሩትን ሞናሞን በላይ፣ ጤናለም ሙላቴ፣ሳምራዊት ቀሬ፣አሳቤ አያል እና የአካባቢው ነዋሪ የሆነችውን ትእግስት መሳይ እንዲሁም ለጊዜው በውል ያልተለዩ ሴቶችን ከ1ኛ እስከ 8ኛ የተገለፁ ተከሳሾች ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ዱላ እና የጦር መሳሪያ ታጥቀው የሚሄዱበትን መኪና መንገድ ላይ አስገድደው በማስቆም 4ኛ ተከሳሽ አወል ጅብሪል የተባለው የመኪናውን ቁልፍ ሲነቅል ሌሎች ተከሳሾች ደግሞ መኪናውን በመፈተሽ የኦሮሚኛ ቋንቋ የማይችሉ ወይም አማርኛ ቋንቋ ብቻ የሚችሉትን በመለየትና ከመኪናው በማስወረድ ጠልፈው ወይም አግተው በአካባቢው ወደሚገኘው ጫካ ይዘው የሄዱና ለኦነግ ሸኔ የበላይ አመራሮች ያስረከቡ በመሆኑ እና 2ኛ) በቀን 25/03/2012ዓ.ም በግምት ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ሲሆን በቄለም ወለጋ ዞን አንፍሎ ወረዳ ሱዲ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የደምቢ ዶሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የተፈጠረውን ግጭት በመፍራት ከደምቢዶሎ ከተማ ወደ ጋምቤላ ከተማ አቅጣጫ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-35138 ኦሮ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተሳፍረው ወደ ቤተሰቦቻቸው በመሄድ ላይ እያሉ የነበሩትን በላይነሽ መኳንንት፣ስርጉት ጌጤ፣ውዴ ግርማው፣ግርማሽ የኔነህ፣አስካሉ(የማታ) ቸኮል፣ግርማው ሀብቴ እና ለጊዜው በውል ያልተለዩ ተማሪዎችን ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ላይ ሲደርሱ ከ9ኛ እስከ 12ኛ የተጠቀሱ ተከሳሾች እና ሌሎችም ለጊዜው ካልታወቁ በርካታ የኦነግ አባላት ግብረ አበሮቻቸው ጋር የጦር መሳሪያና ዱላ ይዘው የሚሄዱበትን መኪና መንገዱ ላይ በማስቆምና መኪናውን በመፈተሽ ኦሮምኛ ቋንቋ የማይችሉ ወይም አማርኛ ቋንቋ ብቻ የሚናገሩትን የመታወቂያ ወረቀታቸውን በማየትና በመለየት 5 ሴቶችና 1 ወንድ የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ከተሽከርካሪው በማውረድና በመደብደብ ጠልፈው ወይም አግተው ለ12ኛ እና 14ኛ ተከሳሾች እንዲሁም ለሌሎች የኦነግ ሽኔ አባላት አስረክበው እነርሱ ደግሞ በበኩላቸው የታገቱትን ተማሪዎች ለጊዜው ላልታወቁ ለኦነግ ሸኔ አመራሮች አስረክበዋል፡፡መልካም ንባብ… Print 372 Documents to download 247066 (.pdf, 973.97 KB) - 132 download(s)