Monday, July 18, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ኮ/ል መንግስቱ ማሩ እና የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ የሰ.መ.ቁ 220703 ጉዳዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች የወንጀል ሕግ ቁጥር 669/2/ለ ድንጋጌን በመተላለፍ ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሱ ለማግኘት በማሰብ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በሲ.ኤም.ሲ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል መከላከል የስራ ባልደረባ ሆኖ ሲሰራ በቀን 27/2/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ሲሆን ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 08 ልዩ ቦታው ሴፍ አየር መንገድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን አስመልክቶ የወ/ሮ ብስራት ሐጎስን መኖሪያ ቤት በሚበረብሩበት ወቅት የግል ተበዳይ ንብረት የሆነውን ግምቱ ብር 15000 የሆነ A 31 ሳምሰንግ ሞባይል የወሰደ በመሆኑ በፈጸመው የስርቆት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ… Print 15227 Documents to download 220703(.pdf, 914.72 KB) - 1208 download(s)