Friday, March 4, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ወ/ሮ ሀለዊያ አብዱጀባር እና እነ ሂላል አበዱጀባር የሰ/መ/ቁ፡-206828 ጉዳዩ እንዲህ ነው፡፡ የአሁን አመልካች ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የአፈፃፀም አቤቱታ ቀደም ሲል ከአሁን ተጠሪዎች ጋር በዚያው ፍርድ ቤት በነበራቸው ክርክር ለክሱ ምክንያት ከሆነው ቤትና ይዞታ ላይ ለአሁን ተጠሪዎች እናት በፍርድ ቤቱ በፀደቀው ስምምነት ላይ ከተጠቀሰው ውጭ ባለው ቤት እና ይዞታ ላይ በስማቸው ካርታ እና ፕላን እንዲሰራላቸው ለክፍሉ ይዞታ አስተዳደር ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ይጠይቃሉ፡፡ ይህንኑ የአፈፃፀም አቤቱታ አስመልክቶ በአሁን ተጠሪዎች በኩል ምን መከራከሪያ እንደቀረበ የስር ፍርድ ቤት መዝገብ አያሳይም፡፡ በሌላ በኩል በዚህ የሰበር ሰሚ ችሎት ክርክር ተካፋይ ያልሆኑት አቶ አህመድ መሃመድ የተባሉት ግለሰብ የአፈፃፀም አቤቱታ የቀረበበት ቤት እና ይዞታ የአሁን ተጠሪዎች እና የራሳቸው አውራሽ የጋራ የውርስ ሀብት መሆኑን ጠቅሰው የአፈፃፀም አቤቱታው ውድቅ እንዲደረግ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ህግ ቁጥር 418 መሰረት አፈፃፀሙን በመቃወም ይቀርባሉ፡፡………. Print 13095 Documents to download 206828(.pdf, 917.35 KB) - 913 download(s)