Friday, July 22, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ወ/ሮ ለምለም ቅጣው እና ወ/ሮ ዘቢባ የሱፍ የሰ/መ/ቁ 214325 ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው የአሁን ተጠሪ በቀን 09/06/2012 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ ሟች አባቴ የሱፍ ኢብራሂም በቀን 05/05/1987 ዓ.ም በሞት ተለይቷል፡፡ የአባቴን ወራሽነት በደዋ ጨፋ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ 0302372 አረጋግጫለሁ፡፡ አባቴ በህይወት ሲኖር ተከሳሽን አግብቶ 6 ልጅ ያላቸው ሲሆን እኔ ደግሞ ከበፊት ሚስቱ ወ/ሮ ሀሊማ ኡስማን የወለደኝ ስሆን አባቴ በህይወት እያለ በከሚሴ ከተማ ውስጥ 528 ካ.ሜ በሆነ ቦታ ላይ የሚገኝ 1 ትልቅ ቆርቆሮ ቤት በውስጡ 2 ክፍል ያለው፣1 ትልቅ ቆርቆሮ ቤት 6 ክፍል ያለው እንዲሁም 6 ክፍል ሰርቪስ ቤት ያለው ሁሉንም በጋራ አፍርተዋል፡፡ አባቴ ሲሞት ህጻን ስለነበርኩ ካደኩኝ በኋላ በተከሳሽ ስር እንደ ወላጅ እናት በማየት በፍርሀትና በማክበር ክስ ሳላቀርብ ቆይቼ ንብረት እንድታካፍለኝ በሽማግሌ ብጠይቅም ለማካፈል እንቢ ስላለች የውርስ ንብረት ድርሻዬን እንድታካፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ……… Print 14124 Documents to download 214325(.pdf, 1.01 MB) - 1105 download(s)