Thursday, July 21, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ወ/ሮ ላምሮት ዘለቀ እና እነ ወ/ሮ መንበረ ወንድምኩን የሰበር መዝገብ ቁጥር 211647 ጉዳዩ በተጠሪዎች መካከል የነበረው እንደባልና ሚስት ግንኙነት በመቋረጡ የግንኙነቱ ውጤት የሆነው የንብረት ክርክር ተደርጎ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ አመልካች ፍርዱን በመቃወም ባቀረቡት አቤቱታ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጀመረ ክርክር ሲሆን ፤ የአመልካች የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ ይዘት በአጭሩ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ጥር 12 ቀን 2002 ዓ/ም በሀገር ባህል ጋብቻ ሲፈፅሙ በዚሁ ዕለት በተደረገ የጋብቻ ውል 2ኛ ተጠሪ ከጋብቻው በፊት በስጦታ ያገኙትን በአዲስ አበባ ከተማ የካ ከፍለ ከተማ ወረዳ 12 በ226 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ያረፈ 20 ቆርቆሮ ቤት እና ከጋብቻ በኋላ የሚያፈሩትን ንብረት የጋራ ለማድረግ ስምምነት ማድረጋቸውንና በጋብቻ ውስጥ እያሉ ብድር ወስደው ተጨማሪ 9 ከፍሎች እና የውጭ በር ማስራታቸውን በመግለፅ የተጠሪዎች የጋራ ሀብት ነው በማለት ፍርድ ያረፈበት ቤትና የቤት ቁሳቀስ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ያፈሩት ንብረት በመሆኑ እነዚህን ንብረቶች አስመልክቶ ፍትሐዊ ውሳኔ ይሰጠኝ የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ……….. Print 14362 Documents to download 211647(.pdf, 1.04 MB) - 1313 download(s)