Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243 ጉዳዩ የውርስ ንብረት እና የሚስትነት ድርሻ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ በጀመረበት በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች 1ኛ ጣ/ገብ ፤ከ1ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተጠሪዎች ከሳሽ፤ከ6ኛ እስከ 13ኛ ያሉ ተጠሪዎች እንዲሁ ጣ/ገብ አመልካች ነበሩ፡፡ አሁን ከ1ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተጠሪዎች አሁን በክርክሩ በሌሉ ሁለት ተከሳሾች ላይ ባቀረቡት ክስ የሟች አባታቸው አቶ ሁሴን አህመድ ንብረት የሆኑና በሟች ስም የሚገኙ 1ኛ/ በስር 1ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኝ በአሊቾ ውሪሮ ወረዳ ቀረሶ ቀበሌ ገሸዴ ተብሎ በሚጠራ መንደር የሚገኝ 3 ጥማድ የእርሻ መሬት፤2ኛ/ በስር 2ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኝ በወልቂጤ ከተማ 01 ቀበሌ የሚገኝ በ1050 ካ.ሜ ላይ ያለ የንግድ ቤት እና ከቤቱ የሚገኝ የኪራይ ገቢ፤3ኛ/ በስር 1ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኝ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 03-21138 የሆነ ዶልፊን ተሽከርካሪ፤ 4ኛ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በደቡብ ግሎባል ባንክ በሟች ስም በተከፈቱ ሂሳቦች የተቀመጠ ገንዘብ የሟች የውርስ ሀብት ስለሆነ በድርሻችን ተከሳሾች ያካፍሉን ሲሉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ… Print 4919 Documents to download 257243(.pdf, 868.34 KB) - 736 download(s)