Friday, December 31, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, Cassation ወ/ሮ ረሂማ አብዱላሂ እና እነ ከዲር ዮሱፍ በከር የሰ/መ/ቁ፡- 202581 ጉዳዩ የጋራ የሆነ የእርሻ መሬት በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደረገ ነዉ የተባለዉ ዉል ቀሪ እንዲደረግና ይዞታዉን ለማስለቀቅ እንዲሁም አላባ ለማስከፈል የቀረበ ክስ የመዳኝት ሥልጣን የሚመለከት ነዉ፡፡ አመልካች በተጠሪዎችና በስር 1ኛ ተከሳሽ አቶ ሙስጠፋ ዩሱፍ ላይ በሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር ለ30 ዓመታት በትዳር ተሳስረን አብረን ስንኖር በሐረር ክልል በድሬ ጠያራ ወረዳ በአቦከር ሙጢ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ዉስጥ ያለንን አንድ ጥማድ ከግማሽ የሆነ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰዉን የእርሻ መሬት ያለእኔ ፈቃድ በሕገ-ወጥ መንገድ ለአሁን ተጠሪዎች በሽያጭ አስተላልፈዋል፡፡ በዚህ ምክንያት በአመት 20 ኩንታል ማሽላ በማምረት ማግኘት የምንችለዉን በኩንታል በብር 1200.00 ሂሳብ ብር 24,000.00 አሳጥዉኛል፡፡እየተቃወምኩ በመሬቱ ላይ ተጠሪዎች ቤት ሰርተዉበታል፡፡ስለሆነም ዉሉ ሕገ-ወጥ ስለሆነ እንዲፈርስና የገነቡትን ቤት አፍርሰዉ ይዞታዬን እንዲለቁ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡…………… Previous Article አቶ አዲሱ ዓለሙ እና ወ/ሮ መስከረም ንጉሴ የሰ/መ/ቁ፡- 202486 Next Article የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን እና እነ ዶ/ር በድሩ ሁሴን የሰ /መ/ቁ፡- 204300 Print 12551 Documents to download 202581(.pdf, 731.34 KB) - 1094 download(s)