/ Categories: CASSATION, Cassation

ወ/ሮ ራሔል ገብረመድህን እና ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የሰ/መ/ቁ 247062

ጉዳዩ የሽያጭ ውልን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በስር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ እና ተጠሪ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡አመልካች ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት ክስ ተጠሪ የኮሮና ወረርሽኝ መከላከያ ቁሳቁሶች ከጉዳዩ አንገብጋቢነት እና አጣዳፊ ከመሆኑ አንፃር ከፌደራል የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በተላለፈለት መመሪያ መሰረት ከመደበኛ የግዥ ስርዓት ውጪ እንዲገዛ ተፈቅዶለት ከአመልካች ላይ ግምታቸው ብር 500,654.67(አምስት መቶ ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ አራት ብር ከ64/100) የሆኑ ቁሳቁሶችን አመልካች ከማስተዳድረው የሰም ፕላስቲክ በቀጥታ ግዥ ገዝቶ በቀን 23/10/2012 ዓ.ም ተረክቦኛል፡፡ ተጠሪ መረከቡንም የሚያሳይ የዕቃዎች ዓይነት ብዛት እና ዋጋቸውን የያዘ የዕቃ ገቢ ማድረጊያ ደረሰኝ ሰጥቶኛል፡፡ ተጠሪ ክፍያ እንዲከፍል ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ክፍያ ሊከፍል ስላልቻለ የዕቃውን ዋጋ ከነወለዱ ብር 545,713.56( አምስት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሰባት መቶ አስራ ሶስት ብር ከ92/100) እንዲከፍል እንዲወሰንላቸው ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…

Print
413

Documents to download

  • 247062(.pdf, 876.53 KB) - 126 download(s)