/ Categories: CASSATION, Cassation

ወ/ሮ ሳፊያ ከድር እና እነ ሐጂ አማን ሐጂ ሁሴን (6ሰዎች) የሠ/መ/ቁጥር 254696

ጉዳዩ የውርስ ድርሻን የሚመለከት ሲሆን ክሱ በቀረበበት ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ባሌ ዞን በርበሬ ወረዳ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ 1ኛ ተጠሪ ተከሳሽ፤ ከ2ኛ እስከ 6ኛ ያሉ ተጠሪዎች ደግሞ ጣልቃ ገብ ተከራካሪዎች ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ ይዘት፡- የ1ኛ ተጠሪ ሚስት የነበሩት እናታቸው ወ/ሮ ነኢማ ሀሚድ በሞት ከዚህ ዓለም መለየታቸውንና የሟች ወራሾች 7(ሰባት) እንደሆኑ ፤ ሟች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር አፍርተዋል የሚሉትን መገኛቸው እና አዋሳኞቹ በክሱ ላይ ከተመለከቱት ከተራ ቁጥር 1-10 ከተዘረዘሩ ንብረቶች የሟች 50% የሚስት ድርሻ መሆኑን በመግለጽ 1ኛ ተጠሪ የውርስ ድርሻቸውን እንዲያክፈሏቸው እንዲወሰንላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…..

Print
4201

Documents to download

  • 254696(.pdf, 884.59 KB) - 582 download(s)