/ Categories: CASSATION, Cassation

ወ/ሮ ቀመሪያ ሁሴን እናሼህ ጀማል ሁሴን የሠ/መ/ቁጥር 254987

ጉዳዩ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማጃንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ በተከሳሽነት ተከራካረዋል፡፡ አመልካች ባቀረቡት ክስ ከተጠሪ ጋር የነበራቸው ጋብቻ በፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ መፍረሱን ተከትሎ ባቀረቡት የፍቺ ውጤት በሆነው የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል አቤቱታ የጋራ ናቸው ካሏቸው ንብረቶች ውስጥ ለሰበር አቤቱታው ምክንያት የሆኑት በአቤቱታው ተራ ቁጥር 5 ሥር የተጠቀሰው በቶሊና ቶካሊ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ በ15 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት ከጓሮ አትክልቶች ያሉት እና ለቤት መሥሪያ የተዘጋጁ 100 ፍልጦች፤እንዲሁም በተራ ቁጥር 7 ከላይ በተጠቀሰው ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ አዋሳኞቹ በክሱ ላይ የተመለከተው የቡና እና የባህር ዛፍ አትክልቶች እና ልዩ እንጨቶች ያሉበት ይዞታ የግራ ቀኙ የጋራ መሆኑን ገልጸው ተጠሪ ድርሻዬን ያካፍሉኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ… 

Print
1783

Documents to download

  • 254987(.pdf, 863.76 KB) - 268 download(s)