/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

ወ/ሮ ትዕግስት ዓለሙ ቢ/አ/ኤ/ካ ኃ/የተ/የግል ማሕበር የጉባ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት፣የጉባ ወረዳ አካባቢ ጥበቃ፣መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ. 161449

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ በጉባ ወረዳ ማንኩሽ ቀበሌ 10 ሄክታር የእርሻ መሬት በ1987 ዓ/ም ተመርቼ በሕጋዊ መንገድ የያዝኩትን 1ኛ ተጠሪ ፈቃድ ሳያወጣ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ትክና ካሣ ሳይከፍሉኝ ያላግባብ የይዞታ መሬቴን ለ1ኛ ተጠሪ በ2008 ዓ/ም ስለሰጡብኝ የ2008/2009 ዓ/ም የምርት ዘመን ያጣሁት የሰሊጥ ምርት ብር 115,000.00፣ ማሳ ለማዘጋጀት ያወጣሁት ብር 40,000.00፣ የማፈናቀያ ካሣ ብር 115,000.00 እና 10 ሄክታር ትክ የእርሻ መሬት እንዲሰጡኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ ያቀረበው መልስ ካሣና ትክ አስተዳደሩ የሚሰጠው እንጂ 1ኛ ተጠሪን አይመለክትም፡፡ በኢንቨስትመንት በሕጋዊ ፈቃድ የተሰጠኝ ስለሆነ ልጠየቅ አይገባም ብሏል፡፡ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በበኩላቸው መሬቱን የሠጠው የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ እንጂ እኛ አይደለንም፡፡ ካሣው የተጋነነ ነው፡፡ ብር 40,000.00 መሬቱን ለማጽዳት ስለመውጣቱ ማስረጃ አልቀረበም፡፡ ለ21 ዓመት መሬቱ ስለታረሰ የሚጸዳ ነገር የለውም፡፡ መሬቱን የሠጠው ቢሮ በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር ይታዘዝልን ብለዋል፡፡ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ  በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር ታዞ ባለመቅረቡ ጉዳዩ በሌለበት ታይቷል፡፡...........

Previous Article በአማጋ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጮራ የጋዝና ኬሚካል ውጤቶች ፋብሪካ፣ሂክማ የፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ ኃ/የተ/የቡድን ኢንተርፐራይዝ እና ሌሎች የሰ-መ-ቁ 175155
Next Article ወ/ሮ ገነት ገሠሰ ቸኮል ፣ የአ/አ ከተማ የየካ ክ/ከተማ አስ/ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ሌሎች የሰ/መ/ቁ 180001
Print
18319