/ Categories: CASSATION, Cassation

ወ/ሮ ነጃት የሱፍ እና እናእነ አቶ አራጋው ካሳው /2ሰዎች/ የሰ/መ/ቁ.ጥር 254909

የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች በ05/03/2016 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የደሴ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.28705 በቀን 27/07/2014 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.55278 በቀን 14/11/2014 ዓ.ም በከፊል ከሻሻለው በኋላ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.0336346 በቀን 16/02/2015 ዓ.ም አሻሽሎ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ አተረጓጎም ስህተትየተፈጸመበትበመሆኑሊታረምይገባልበማለታቸውሲሆንበስርፍ/ቤትየአሁን አመልካችከሳሽ ሆነው 1ኛ ተጠሪተከሳሽበሆኑበት የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ክስ 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ ሆነው ሆነው የቤት ሽያጭን በተመለከተ ጉዳይተከራክረዋል፡፡ አመልካች በስር ፍ/ቤት በቀን 05/04/2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ ከተጠሪ ጋር ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2009 ዓ.ም ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደ ባልና ሚስት ሆነው ከሃምሌ 10 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ጋብቻ ፈጽመው ሲኖሩ የነበረ መሆኑን፤ በደሴ ከተማ የሚገኝ አዋሳኙ በክሳቸው የተጠቀሰ በተጠሪ ስም የተመዘገበ ግምቱ ብር 2,500,000.00(ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ)የሆነ ሰርቪስ ያለው ቤት፣ በባንክ ውስጥ በተጠሪ ስም በተከፈተ  ሂሳብ የተቀመጠ ገንዘብ እንዲሁም የተለያዩ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ያላቸው መሆኑን፣ሆኖምተጠሪ ቤቱን ያለ አመልካች እውቅና ሽጦ የስመ ንብረት ዝውውር ሊያደርግ በሂደት ላይ እያለ አመልካች ባቀረቡት ተቃውሞ ሽያጩ ሊቆም መቻሉን ገልጸው ጋብቻው ፈርሶ ተጠሪ እነዚህን የጋራ ንብረቶች እንዲያካፍላቸውና የግላቸው የሆኑ ንብረቶችን እንዲመልስላቸው ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ ….

Print
500

Documents to download

  • 254909(.pdf, 1.05 MB) - 116 download(s)