/ Categories: CASSATION, Cassation

ወ/ሮ ነጻነት ኪዳነማርያም አለነ እና አቶ አበራ በለጠ የሰ/መ/ቁ. 228545

ጉዳዩ የባልና ሚስት ጋብቻ ፍቺን ተከትሎ የቀረበን የጋራ ንብረት ክፍፍል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የአሁን አመልካች በግራቀኙ መካከል የተደረገው ጋብቻ በ03/02/12 ዓ.ም በተሰጠ ውሳኔ መፍረሱን ተከትሎ በጋብቻ ወቅት ላፈሯት ልጃቸው የተወሰነው ቀለብ እንዲሻሻል እና የንብረት ክፍፍል እንዲደረግ የጠየቁ ሲሆን ይኸውም 1ኛ በተጠሪ ስም በካርታ ቁ የካ 246/183777/07 የተመዘገበ በየካ ክ/ከ/ ወረዳ 11 የቤት ቁ 062 የቦታ ስፋት 452 ካ.ሜ የሆነ ይዞታና ቤት 2ኛ. በተጠሪ ስም በካርታ ቁ AA000080106415 የተመዘገበ በን/ላ/ክ/ከ ወረዳ 01 የቤት ቁ አዲስ ይዞታና ቤት 3ኛ. በተጠሪ ስም ተመዘገበ የካ ክ/ከ ወረዳ 12 የካ አባዶ የሚገኝ የቤት ቁጥር አዲስ ስፋቱ 885 ካ.ሜ ይዞታና ቤት እናዲሁም 4ኛ. ተጠሪ በመንደር ውል ገዝቶ ውክልና ተቀብሎ የብድር ውል የተዋዋለበት በአቶ ኮዴ ቢተማ ስም የተመዘገበ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ቢፍቱ ሚሽን ቀበሌ 04 የቤት ቁጥር የሌለው 140 ካ.ሜ G+3 ቤት እንዲሁም ከፍቺ ውሳኔ 6 ወር በፊት የተለያየን ሲሆን በተራ ቁ 1 የተገለጸው ቤት ለእህቱ በወር ብር 7,000 የሚከራይ በመሆኑ በወቅቱ ዋጋ ተገምቶ እንዲከፍለኝ በተራ ቁጥር 2 ለወፍጮ ቤት የተከራየ በመሆኑ ብር 14,000 እንዲሁም ለጸጉር ቤት ብር 4,000፣ ለሸቀጣ ሸቀጥ ብር 3,000፣ በተራ ቁ. 3 የተጠቀሰው ውስጥ የሚገኝ አንድ ክፍል ቤት ኪራይ በወር ብር 2,500 በመሆኑ የሚገኘው የኪራይ ገቢ አንድንካፈለኝ ይወሰንልኝ የሚል ነው ፡፡መልካም ንባብ…

Print
2812

Documents to download

  • 228545(.pdf, 650.76 KB) - 696 download(s)