Monday, June 6, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ወ/ሮ አሰለፈች ዘነበ እና አቶ ቀጸላ አበበ የሰ/መ/ቁጥር 205500 ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች መጋቢት 26 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 03-91413 የካቲት 11 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታዋን በማቅረቧ ነው፡፡ ቅሬታዋም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የምትቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የምትለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የአሁን አመልካች ከተጠሪ ጋር በጋራ የፈራሁትን የጋራ ንብረት የተጠሪ የግል ንብረት የሚያደርገውንና የግል ንብረቴን የጋራ የሚያደርገውን በወረዳ ፍ/ቤት የጸደቀው ስምምነት መብቴን የሚጎዳ ለህሊናና ለሞራል ተቃራኒ ሆኖ እያለ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 3316 መሰረት ፈራሽ መሆን ሲገባ ስምምነቱ መፍረስ የለበትም ብሎ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዲሁም የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 0391413 እና 03-94947 ላይ በአንድ ጉዳይ የተለያዩ ውሳኔዎች በመስጠቱ ውሳኔዎቹ የሚቃረኑና ተፈጻሚነት የማይኖራቸው በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ………. Print 7649 Documents to download 205500(.pdf, 1.21 MB) - 706 download(s)