/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

ወ/ሮ አበበች ኤጄታ እና አቶ ማሞ ኡርጌሳ የመ.ቁ.211085

ጉዳዩ የገጠር እርሻ መሬት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት የቀረበውም በአሁን አመልካች እና በተጠሪ አውራሾች መካከል የሽያጭ ውል አለ በሚል መነሻነት አመልካች ያቀረቡት የይርጋ ክርክር ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ከይርጋ መቃወሚያው ጋር በተያያዘ በስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ ከተረጋገጠው ነጥብ አኳያ መርምሮ ለመወሰን ነው፡፡ 

ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ሸዋ ዞን ቶኬ ኩታዬ ወረዳ ፍርድ ቤት በአሁን አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው፡፡ ከክሱም ጭብጥ ቦታ እና አዋሳኙ በክሱ ዝርዝር የተመለከተውን ከአያቶቼ በውርስ ሊተላለፍልኝ የሚገባውን የገጠር መሬት አመልካች በግዥ አግኝቻለሁ በሚል ምክንያት ይዘው አለቅም ያሉኝ በመሆኑ በፍርድ ኃይል ተገደው ሊለቁልኝ ይገባል የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ……….

Print
8756

Documents to download

  • 211085(.pdf, 860.59 KB) - 698 download(s)