Thursday, June 5, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ወ/ሮ አዳነች ሞኝነት እና አቶ ይልቃል አቤ የሰ.መ.ቁ 250332 ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነው ክርክር የተጀመረው በአማራ ክልል ባሶ ሊበን ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን በወረዳው ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ በባሶ ሊበን ወረዳ ፍርድ ቤት ላይ ባቀረቡት ክስ አመልካች የተጠሪ አያት የሟች እማሆይ ጥሩ በላይ የቤተሰብ አባል ሳትሆንና ከሟቿ ጋር በአንድ ላይ ሆኖም ሆነ ከውጭ ሆኖ ሟቿን ሳትጦርና ሳትንከባከብ እንደጦረች እንደተንከባከበችና የሟቿ የቤተሰብ አባል እንደሆነች አስመስላ የሟቿን የእድሜ ባለፀጋነትን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሟቿ ከቢሮ ሳይሄዱ እንደሄዱና በስጦታ እንዳስተላለፉላት በማድረግ ከመሬት ባለሙያ ጋር በመመሳጠር በ13/10/1998ዓ.ም የስጦታ ውል በማስሞላት የኑዛዜ ስጦታውን በመሬት አስተዳደር ጽ/ቤት በማስመዝገብ የኑዛዜ ስጦታ አለኝ በማለት አጭበርብራ ማስረጃ እንደያዘች” ገልጸው የመሬት ስጦታ ውሉም ሆነ ማስረጃው እንዲሰረዝላቸው ዳኝነት በመጠየቅ ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…. Print 5566 Documents to download 250332(.pdf, 886.35 KB) - 793 download(s)