Tuesday, May 20, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ወ/ሮ እሌኒ ነጋሽ ኪዳኑ እና አቶ ክብሮም ገ/መድህን ወርቅነህ-የሰበር መ/ቁ 250505 ጉዳዩ የቤት ኪራይ ውልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውየፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞተከሳሽ ነበሩ፡፡ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ይዘትበለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር አዲስ የካርታ ቁጥር ጨ-3062/96 የሆነ ቤት ተጠሪ ለሆቴል አገልግሎት እንዲጠቀምበት ከቀን 30/06/2010 ዓ.ም ጀምሮ ለ5 አመት በወር ብር 60,000 በ4ኛውና 5ኛው አመት የኪራዩን ገንዘብ 75,000 ብር በማድረግ የኪራይ ውል ስምምነት እንዳደረጉና ነገር ግን ተጠሪ የውል ግዴታውን ባለመወጣቱ አመልካች ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክስ አቅርበው በመ/ቁ 126817 በቀን 14/12/13 ዓ.ም ቤቱን እንዲለቅና ያልከፈለውን ተርን ኦቨር ታክስ እንዲከፍል ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ በአፈጻጸም ሂደት ላይ እያለ ተጠሪ ይግባኝ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 279740 አቅርበው ፍርድ ቤቱም ተጠሪ ቤቱን ሊለቁ አይገባም በሚል የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር ውሳኔ የሰጠ ቢሆንም ተጠሪ በገዛ በፍቃዱ ታሕሳስ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ቤቱን ለቆ ወጥቷል፡፡ ስለሆነም ከሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም እስከ ታሕሳስ ወር 2014 ዓ.ም የቤት ኪራይ ሒሳብ ብር 435,000 እና የተጠቀመበት የታህሳስ ወር የውኃ ፍጆታ ብር 5,643 እና የተርን ኦቨር ታክስ ከሚያዝያ 27/2013 እስከ ታህሳስ 24/2014ዓ.ም 8,700 እንዲሁም ተጠሪ የተከራየውን ቤት ሲለቅ በተረከበበት ሁኔታ ለማስረከብ ቢስማማም በቤቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ በመሆኑ ጉዳቶቹንም ዘርዝው በማቅረብ ለተበላሸው ቤት ወደነበረበት ለመመለስ ብር 303,400 እንዲከፍለኝ እንዲወሰን በሚል ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ …. Print 5302 Documents to download 250505(.pdf, 1.05 MB) - 534 download(s)