Tuesday, May 13, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ወ/ሮ እቴነሽ እምቢበል እና እና አቶ ሮበንነዳሳ /4ሰዎች የሰ/መ/ቁ 259445 አመልካች በቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ የቡና እና ቅመማቅመም ልማት ድርጅትን በተመለከተ ያደረጉት ውል እንዲፈርስ እና በተጠሪዎች ዕጅ የሚገኘው የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር፣ የኢንቨስትመንት ሰርተፍኬት ፤ እንዲሁም በቀበሌ በኩል የተዘጋጀ ቨርቫል እንዲመለስላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር መርምሮ በመዝገ ብቁጥር 23376 ሀምሌ 14/2015 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ በውል ሰነዱ ላይ ሻጮች ብቻ ፈርመው ገዥዎች ያልፈረሙበት መሆኑን፤እንዲሁም 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች የውጭ ሀገር ዜጋ መሆናቸው ስለተረጋገጠና በህጉ የመሬት ባለሃብት መሆን ስለማይችሉ ውሉ ሊፈርስ ይገባል፤ ገዥዎች ለሻጭ የከፈሉት የቀብድ አጠፌታ እና ተጨማሪ ክፍያ በጠቅላላው ብር 550,000.00 (አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ) እንዲመለስላቸው፤ እንዲሁም የተጠየቁት ሰነዶች ለአመልካች እንዲመለሱ በማለት ወስኗል፡፡ በዚህው ሳኔ የአሁን ተጠሪዎች ቅርተሰኝተው ይግባኝ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዋል፡፡ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የይግባኝ ክርክሩን መርምሮ ከፍሲል በመግቢያችን በገለጽነው ቀን በሰጠው ውሳኔ ግራ ቀኙ በውላቸው ላይ ግዴታቸውን ለመወጣት ካስቀመጡት የሁለት ወር ጊዜ ገደብ አኳያ የአሁን አመልካች የሰጡት የማስጠንቀቂያ ጊዜ ተጠሪዎች ቀርበው ግዴታቸውን ለመፈፀም በቂ ባለመሆኑ ተጠሪዎች እንደው ሉግዴታቸውን አልተወጡም ተብሎ ውሉ ሊፈርስ አይገባም በማለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ሽሯል፡፡ መልካም ንባብ …. Print 383 Documents to download 259445(.pdf, 1.01 MB) - 142 download(s)