Friday, March 4, 2022 / Categories: CASSATION, Cassation ወ/ሮ ከድራ ጂብሪል አበዲድ እና ወ/ሮ ሀዲዮ ኬይሬ የሰ/መ/ቁ፡-202693 የአሁን ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአሁን አመልካች እና በስር 2ኛ የፍርድ ባለዕዳ ላይ ባቀረቡት የአፈፃፀም ክስ ባቀረብኩት የወራሽነት አቤቱታ መሰረት ጉዳዪ በአጣሪዎች ከተጣራ በኋላ የውርስ ሀብት ነው ተብሎ በተወሰነልኝ መሰረት ይዞታው የውርስ ሀብቴ መሆኑ በተረጋገጠው መሰረት እንዲፈፀምልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡አመልካች በሰጡት መልስም በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 188/92 አንቀጽ 4(2) መሰረት በፍርድ ቤት ቀርበን ለመዳኘት አንፈልግም በማለት ያመለከትን በመሆኑ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ዘግቶ ማሰናበት ሲችል ጉዳዪን ማየት የለበትም፡፡ጉዳዩን ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት አቅርበን ታይቶ የመጨረሻ እልባት ያገኘ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ዘግቶ ሊያሰናብተኝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡……… Print 11774 Documents to download 202693(.pdf, 928.19 KB) - 1171 download(s)