/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

ወ/ሮ ወይንሸት ወርቁ ጅማ እና አቶ ፈይሳ ኃይሌ ሮቢ የሰ.መ.ቁ 213041

የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የሲናና ወረዳ ፍ/ቤት 2ኛ ከሳሽ ሆነው፤ አሁን ሰበር ክርክሩ ላይ የሌሉት ፈቃዱ ስሜ(የስር 1ኛ ከሳሽ)፤ ብርሃኑ ኃይሌ(ስር 3ኛ ከሳሽ) ሆነው በተጠሪ(ስር 2ኛ ተከሳሽ) እና አሁን ሰበር ክርክሩ ላይ በሌሉት ወ/ሮ ደሚቱ ሮቢ(ስር 1ኛ ተከሳሽ) ላይ ባቀረቡት ክስ ለስር 1ኛ ተከሳሽ አያታችን ወ/ሮ ኡርጎ ጂማ አክስቷ ሲሆኑ፤ ተጠሪ(ስር 2ኛ ተከሳሽ) ደግሞ የአያታችን የልጅ ልጅ ሲሆን አያታችን ወ/ሮ ኡርጎ ጂማ በ24/1/10ዓ.ም ሞታለች፡፡ ሟች አያታችን ያላት ልጆች 4 ይኀውም የስር 1ኛ ተከሳሽ አባት፤ ኃይሌ ሮቢ፤ የስር 1ኛ ከሳሽ አባት ስሜ መርጋ፤ የአመልካች(ስር 2ኛ ከሳሽ) እናት ሙሉ ሮቢ እና የስር 3ኛ ከሳሽ እናት ዘውዲቱ ሮቢ ናቸው፡፡ የአያታችን ልጆች አራቱም በህይወት ስለሌሉ የአያታችን ወራሾች መሆናችን ተረጋግጦ አከራካሪውን በተጠሪ(ስር 2ኛተከሳሽ) እጅ የሚገኝ በሮቤ ከተማ በኦዳ ሮቤ ቀበሌ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት እንዲሁም በክሱ ከተራ ቁጥር 2ኛ-6ኛ ስፋቱና አዋሳኙ የተገለጸው የእርሻ መሬት እንዲሁም በተጠሪ እና በስር 1ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኝ ኦንሾ በሚባል አካባቢ የሚገኝ ስፋቱ 16 ጥማድ የሚሆን እና አንድ ሺህ እግር ባህርዛፍ የሚገኝበትን  በማለት እንዲሁም ሌሎች የእርሻ መሬት እና መኖሪያ ቤት በመዘርዘር አያታችን ከተከሳሾች ጋር ስትጠቀምበት ቆይታ ለወራሾቹ የሚገባውን እና ስር ከሳሾች በቤተሰባችን ምትክ አያታችንን መውረስ እንድንችል እንዲረጋገጥልን እና ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ሀብትና ይዞታ ከመሰረቱ የአያታችን መሆኑ እንዲወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ……    

Print
12602

Documents to download

  • 213041(.pdf, 826.79 KB) - 1021 download(s)