/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

ወ/ሮ ደባሽ ማሞ እና አቶ አባይ ዘውዴ የሰበር መዝገብ ቁጥር 205045

ጉዳዩ ዳግም ዳኝነትን የተመለከተ ሲሆን አመልካች የዳግም ዳኝነቱን አቤቱታ ያቀረቡት ለገምዛ ንዑስ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን የአቤቱታው ይዘት፡- ቀደም ሲል መገኛው እና አዋሳኞቹ በአቤቱታው ላይ የተገለፀው የገጠር መሬት ይዞታ ተጠሪ የአባቴ ነው በማለት የይዞታ መሬት ይገባኛል ክስ በአመልካች ላይ አቅርቦ ፤ ፍርድ ቤቱም ግራቀኙን አከራክሮ ከክፍሉ ወረዳ የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት ማስረጃ ጠይቆ ጽ/ቤቱም በቁጥር ኤ/ገ/ወ/አስ/5042/001 ግንቦት 21 ቀን 2009 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ ለግራቀኙ ክርክር መነሻ የሆነው ይዞታ መሬት በ1989 ዓ/ም በተደረገው የመሬት ቆጠራ በሟች አቶ ዘውዴ ለማ እና በወ/ሮ ማስረሻ አዲሴ ስም የተቆጠረ ነው በማለት ማስረጃ የሰጠ ሲሆን ፤ ፍርድ ቤቱም ይህንን ማስረጃ መሰረት በማድረግ የሟች ዘውዴ ለማ ድርሻን አመልካች ለተጠሪ እንድታካፍል  የወሰነ ሲሆን ፤ ፍርድ ቤቱ ለውሳኔው መሰረት ያደረገው በተጭበረበረ መንገድ በሀሰት ከወረዳው የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም የተገኘ ማስረጃን መሰረት ያደረገ ሲሆን ፤ ለክርክሩ መነሻ የሆነው መሬት የሟች አቶ ዘወዴ ለማ ሳይሆን የአመልካች መሆኑን ጥር 4 ቀን 2011 ዓ/ም ባገኙት አዲስ ማስረጃ እንዳወቁ ገልፀው ፤ ቀደም ሲል የተሰጠው ውሳኔ በዳግም ዳኝነት ታይቶ እንዲታረም ጠይቀዋል፡፡ ተጠሪም በመልሳቸው፡- አመልካች ጥር 04 ቀን 2011 ዓ/ም አገኘሁ በማለት ያቀረቡት ማስረጃ የተገኘው ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ/ም ስለሆነ አዲስ የተባለው ማስረጃ ከተገኘ ከአንድ ወር በኋላ የቀረበ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ፤ ቀደም ሲል ይዞታ መሬቱን አስመልክቶ የተሰጠው ውሳኔ በተጭበረበረ መንገድ የተገኘ አለመሆኑን ፤ አመልካች አገኘሁ የሚሉት ማስረጃም በአዲስ እንደተገኘ የሚቆጠር ባለመሆኑ ጉዳዩ በዳግም ዳኝነት ሊታይ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡መልካም ንባብ……….

Print
8467

Documents to download

  • 205045(.pdf, 1.03 MB) - 717 download(s)