Friday, March 4, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ወ/ሮ ዱሬቲ ረያድ እና አቶ መሐመድ ቱኬ የሰ/መ/ቁ፡-206988 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 335988 መጋቢት 6ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችሎት ጉዳዩን በየደረጃው የተመረመሩት የክልሉ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔና ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈፀመበትም ሲል የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብሎ እንዲታረምላቸው አመልካች በመጠየቃቸው ነው፡፡ በምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጀመረው የአፈፃፀም ክርክር የአሁን አመልካች የወ/ሮ ትግስት ግርማ ወራሾች ሞግዚት ሆነው የአፈፃፀም ክርክር ጣልቃ ገብ፣ የአሁን ተጠሪ የፍርድ ባለመብት፣ አቶ ሪያድ መሐመድ (የአመልካች አባት) የፍርድ ባለዕዳ፣ ሀዋስ ሀጅ ሁሴን(የአቶ ሪያድ መሀመድ ባለቤት) ደግሞ ሁለተኛ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የፍርድ ባለመብት የሆኑት ተጠሪ የፍርድ ባለዕዳው 1,785,000.00ብር እንዲከፍለው የተወሰነበትን ፍርድ ለማስፈፀም በሻሸመኔ ከተማ የሚገኙ ሁለት ቤቶች የፍርድ ባለዕዳው ንብረት ናቸው ተብለው ቤቶችን ለመሸጥ ጨረታ ሲወጣ ከእነዚህ ቤቶች መካከል በ350 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ቤት የሟች እናታቸው የወ/ሮ ትዕግስት ግርማ ድርሻ ያለበት እና የፍርድ ባለዕዳ የሆኑት አባታቸው ድርሻቸውን ለእነሱ ያስተላለፈላቸው መሆኑን በመዘርዘር ጨረታው እንዲሰረዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 418 መሰረት አመልካች መቃወሚያ አቅርበዋል፡፡ ሁለተኛ ጣልቃ ገብ ደግሞ በዚሁ ከተማ በ180 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራው ቤት ለፍርድ ማስፈፀሚያነት እንዲውል ለመሸጥ ጨረታ መውጣቱን በመቃወም አቤቱታ አቅርበዋል፡፡…….. Print 12942 Documents to download 206988(.pdf, 930.76 KB) - 903 download(s)