/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

ወ/ሮ ጡባ ሣቢር እና አቶ መሐመድ አደም የሰ/መ/ቁጥር 210592

ጉዳዩ በፍርድ አፈፃፀምን ወቅት የተጋቢዎች የጋራ ንብረት የሆነ ቤት የሚከፈልበትን መንገድ የሚመለከት ክርክር ነው፡፡ በስር ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ፍርድ ቤት በተጀመረው የአፈፃፀም ክርክር ተጠሪ የአፈፃፀም ከሣሽ አመልካች ደግሞ የአፈፃፀም ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

አመልካችና ተጠሪ ተጋቢዎች ሆነው በትዳር ከቆዩ በኋላ የነበራቸው ትዳር በፍቺ ሲፈርስ በገጠርና በከተማ የነበራቸው የጋራ ንብረት ክፍፍል አድርገው ነገር ግን በቡታጅራ ከተማ እሬሻ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የጋራ ቤታውቸውን እንዲካፈሉ ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ ለአፈፃፀም እንዲመች ማዘጋጃ ቤቱ ገምቶ እንዲያቀርብ በመታዘዙ ግምቱ ተሰርቶ ከቀረበ  ተሸጦ እንዲካፈሉ ከተወሰነ በኋላ ቤቱ ሰነድ አልባ በመሆኑ ጨረታ ሊወጣበት እንደማይችል በመረጋገጡ ሰነድ እስኪወጣበት ድረስ አመልካች የጋራ ልጆቻቸውን ይዛ እየኖረችበት የጋራ ሀብትነት እንዲቆይ ተወስኖ የቆየ ቢሆንም ሰነዱ ስለተሟላ ተጠሪው ቤቱ እንዲከፈልለት አቤቱታውን ለስር ወረዳ ፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡መልካም ንባብ……….

Print
8672

Documents to download

  • 210592(.pdf, 815.24 KB) - 705 download(s)