Friday, July 22, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ወ/ሮ ጽጌ ጅማ እና እነ አቶ ፀጋዬ ፈሲሳ የሰ.መ.ቁ.215435 የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን ተጠሪዎች (የሥር አመልካቾች) በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት ሟች አባታችን አቶ ፈሲሳ ሉቤ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 1 የቤት ቁ.161 ውስጥ እየኖሩ ባደረባቸዉ ሕመም ምክንያት በ13/10/1959 ዓ.ም ከዚህ ዓላም በሞት የተለዩ በመሆኑ፣ የሟች የውርስ ሀብት እንዲጣራልን በማለት ዳኝነት የጠየቁ ሲሆን፤ በፍ/ቤት የውርስ አጣሪዉ ተሹሞ የዉርስ ሀብቱ ተጣርቶ ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ የአሁን አመልካች (የሥር ጣልቃ ገብ) ለይግባኝ ሰሚዉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርባ ፍ/ቤቱም ባሳለፈዉ ዉሳኔ ጣልቃ ገብ ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ በቅድሚያ በማከራከርና ወደ ፍሬ ነገር የሚያስገባም ከሆነ አከራካሪዉ ቤትና ይዞታ ሟችና ጣልቃ ገብ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ የጋራ ሀብት መሆን አለመሆኑ ግራ ቀኙን እንደገና እንዲያከራክርና የመሰለዉን ዉሳኔ እንዲሰጥበት ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መልሶለታል፡፡መልካም ንባብ….. Print 14143 Documents to download 215435(.pdf, 1.03 MB) - 1000 download(s)