/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

ወ/ሮ ፋኖስ ባይልኝ እና እነ ወ/ሮ ፋኖስ ባይልኝ የሰ/መ/ቁ 215524

ከሳሾች ባቀረቡት አቤቱታ ወላጅ አባታችን አስር አለቃ ሞገስ ጋሻው ከዚህ አለም በሞት ስለተለዩ የውርስ ሀብት እንዲጣራ ውርስ አጣሪ እንዲሾምልን በማለት ጠይቀው ተከሳሾችም ክርክራቸውን አቅርበው ውርሱ ተጣርቶ ሪፖርቱ ጥቅምት 24/2009 ዓ.ም ተዘጋጅቶ ቀርቦ ፍ/ቤቱ የውርስ አጣሪ ሪፖርቱን በማረም አጽድቆታል፡፡ በዚህ ውሳኔ ላይ በይግባኝ እስከ ፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ደርሶ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በመ/ቁ 177586 ግንቦት 26 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለ ችሎት የስር ፍርድ ቤቶች አከራካሪውን  የቤት ቁጥር 1285 የሆነ መኖሪያ ቤት በተመለከተ የሰጡትን ውሳኔ በመሻር ጉዳዩ ተጣርቶ እንዲወሰን ጭብጥ ለይቶ በመመሪያ ወደ ስር ፍርድ ቤት መልሷል፡፡ መመሪያ የተሰጠውም የአሁን አመልካች ከሟች ባለቤታቸው ፲ አለቃ ሞገስ ጋሻው በትዳር ሲኖሩ ለክርክር መነሻ የሆነውን የቤት ቁጥር 1285 የሆነ መኖሪያ ቤት በጋራ ያፈሩት ንብረት መሆን አለመሆኑን የግራቀኙን ማስረጃ እራሱ ፍርድ ቤቱ ሰምቶና ተገቢውን ማጣራት አድርጎ ውሳኔ እንዲሰጥበት በሚል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 343(1) ነው፡፡ መልካም ንባብ……..

Print
10779

Documents to download

  • 215524(.pdf, 1.03 MB) - 783 download(s)