/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

ወ/ሮ ፍቅርተ በላይነህ እና እነ ተማሪ ኃይልዬ አበበ የሰበር መዝገብ ቁጥር 204830

አከራካሪውን ይዞታ ለአመልካች በውርስ የተላለፈ ለመሆኑ የይዞታ ማረጋገጫ የቀረበ ከመሆኑም በላይ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚው ችሎት የ1ኛ ተጠሪ እናት እና 2ኛ ተጠሪ በአከራካሪው ይዞታ ላይ መብት የሌላቸው መሆኑን ወስኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤት ቀድሞ ክርክር የተደረገበት ይዞታ እና ለአሁኑ ክርክር ምክንያት የሆነው ይዞታ አንድ ነው ወይስ የተለያዩ የሚለውን ጭብጥ በተገቢው ሳያጣራ ፤ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው መኖሪያ ቦታ የወልደ ህይወት ወልደ ገብርኤል መሆኑ እንዲሁም ሟች አይናለም በላይነህ ወራሽ መሆኗን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በሌለበት ፤ የባሶና ወራና ወረዳ የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት አስቀድሞ በነበረው ክርክር አከራካሪው ይዞታ የወልደ ሕይወት ወልደ ገብርኤል እና ሌሎች ሁለት ወንድሞቹ የጋራ መኖሪያ በመሆኑ 2ኛ ተጠሪ እና ሟች አይናለም በይዞታው ላይ መብት እና ጥቅም የላቸውም በማለት ከሰጠው ማስረጃ የተለየ ማስረጃ ሰጥቶ እያለ ሳይጣራ ሟች አይናለም እና 2ኛ ተጠሪ በመሬቱ ላይ ምንም የተቋቋመ መብት የሌላቸው መሆኑን አስቀድሞ የሰጠውን ውሳኔ የምሽር ውሳኔ መስጠቱ ስህተት ሆኖ ፤ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚው ችሎትም ይህንኑ ጭብጥ ለማጣራት መዝገቡ ያስቀርባል ቢልም ምንም ማጣራት ሳያደርግ ተመሳሳይ ውሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት አመልካች መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ/ም ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መዝገቡ ለችሎቱ ቀርቧል፡፡መልካም ንባብ……….

Print
10019

Documents to download

  • 204830(.pdf, 826.08 KB) - 702 download(s)