/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

ወ-ሮ በድሪያ ዳውድ እና አቶ በርገና መሃመድ የሰ-መ-ቁ 184428

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች በቀን 03/02/2012 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 13570 በቀን 28/12/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው፡፡ ክርክሩ የጀመረው በስር የስልጤ ዞን በሳንኩራ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሰሽ ነበሩ፡፡ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው በወረዳ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች በቀን 22/04/2011 ዓ.ም ባቀረቡት  አቤቱታ ተከሳሽ በወረዳው ልዩ ስሙ ሀያት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ ዘጠኝ ጥማድ መሬት ባለቤቴ ከሀይለ ስላሴ ግዜ ጀምሮ የያዘውና በደርግ ዘመን መሬት ለአራሽ ከተባለ በኋላም 1978 ዓ.ም አካባቢ ከእኔ ጋር ትዳር መስርተን በመሬቱ አብረን እየተጠቀምንበት ቤት ሰርተን ልጅ ወልደን በ1990 ዓ.ም ባለቤቴ ዘመድ ጥየቃ ብሎ ወደ ሀድያ ዞን ሲሄድ የተጠቀሰውን መሬት፣ አንድ በሬና እኔን ከነልጄ አደራ ብሎ ሔዶ ሊመለስ አልቻለም፤ ተከሳሽም በተጣለበት አደራ መሰረት መሬቱን ለግማሽ እያረሰ እየበላን ቆይቶ መጀመሪያ መሬቱ ላይ የነበረው ቤት የፈረሰ በመሆኑ መኪዬ ሰይድ የተባለ ግለሰብ ሌላ ቤት ሰርቶልኝ እየኖርኩ 2002 ዓ.ም አካባቢ በንፋስ በመውደቁ ድጋሚ ሊሰራልን ሲል ተከሳሽ በመከልከል ከራሱ ጋር እንድቀመጥ አድርጎ እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ መሬቱን እያረሰ ቀለቤን እየሰጠኝ ከቆየ በኋላ በሬዬንም ሽጦ ለግልጥቅሙ በማዋልና የእኔን አቅመ ደካማነት መስማትና መናገር የማልችል ረዳት የሌለኝ መሆኔን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም መሬቱን በራሱ ስር በማድረግ ከኖርኩበት ቤት ከእነልጄ አፈናቅሎኝ በሽማግሌ ሲጠየቅ ከሳሽ ያላት ሁለት ጥማድ መሬት ብቻ ነው በማለት እሱንም ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ስለሆነም አላግባብ የያዘውን መሬት እንዲለቅ፤ መሬቱ በስድስት አመት ውስጥ ቢከራይ ሊያወጣ የሚችለውን ዋጋ ብር 43,000.00 (አርባ ሶስት ሺህ)፣ ሽጦ ለግል ጥቅሙ ያዋለው የበሬ ዋጋ ብር 5000.00 (አምስት ሺህ)፣ ከቤት ንብረቴ አፈናቅሎኝ ለተለያየ እንግልት ለዳረገበት ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) የሞራል ካሳ እና ለክስ ያወጣሁት ብር 5000.00 (አምስት ሺህ) በአጠቃላይ ድምር ብር 63,000.00 (ስልሳ ሶስት ሺህ) እንዲከፍለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡……….

Previous Article እነ አቶ ብርቄ ደስታ፣ወ-ሮ ላቀች ገብረወልድ እና ወ-ሮ ፈለቀች በልሄ የሰ-መ-ቁ 189274
Next Article እነ አቶ አድማስ አደመ ከ የባህደር ዙሪያ ወረዳ የገጠር መሬት አስተዳደር ፅ/ቤት የሰ/መ/ቁጥር 189495
Print
15396