Friday, June 4, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation ወ-ሮ አበባዬ ጌቶ እና ወ-ሮ ወርቅዬ ጌቶ የሰ-መ-ቁ 187253 ጉዳዩ የገጠር መሬት ክርክር የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ክልል በሳይንት ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ላይ ያቀረበችዉ ክስ የወላጅ እናቴ አበቡ ወርቁ ወራሽ መሆኔን በ14/09/2010 ዓ.ም አረጋግጫለሁ፡፡ስለዚህ ተጠሪ አራት ቦታ የሚገኝ የውርስ መሬት እንዲታካፍለኝ እንዲወሰንልኝ የሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩሏ ያቀረበችዉ መልስ እናታችን እንደሞተች በ2004ዓ.ም በፍርድ ቤት ስናሳውጅ የአሁኗ አመልካች መሬት ስላላት መሬት አትወርስም ተብላ ተከልክላለች፣አዲሱ አዋጅ ስለሚፈቅድላት አሁን ሊትጠይቅ አይገባም፣በይዞታዉ ላይ የማረጋገጫ ደብተር አውጥቼበት የራሴ መሬት ነው በማለት ክሱ ተቀባይነት እንደሌለዉ ተከራክራለች፡፡ ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክር እና የቀረበውን ማስረጃ መርምሮ እናታቸው ከሞተች ከኋላ እስከ 2009 ዓ.ም ተጠሪ እያረሰች ለሌሎች ወራሾች ስታካፍላቸው የኖረች እና በጽሁፍ የተደረገ የንብረት ክፍፍል ስምምነት ባይኖርም መሬቶቹ የእናታቸው መሆኑ ስለተረጋገጠ ተጠሪ እና አመልካች የማረጋገጫ ደብተር ይዘዉ አላባ ሲጠቀሙ ነበር አመልካች ወራሽ መሆኗ ስለተረጋገጠ ከተጠቀሱት መሬቶች ላይ አመልካች የድርሻዋን ልትካፈል ይገባል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡…………….. Previous Article የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ከ ኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ Next Article እነ አቶ ሐይሌ ንማኒ፣አቶ ነስሩ አህመድ፣ጀማል ዋበላ እና ወ/ሪት ምንዳዬ ለገሰ የሰ-መ-ቁ-188293 Print 16271 Documents to download ወ-ሮ አበባዬ ጌቶ እና ወ-ሮ ወርቅዬ ጌቶ የሰ-መ-ቁ 187253(.pdf, 519.71 KB) - 1141 download(s)