/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

ዘመናይ ጌታቸው አልታሰብ እና ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሰ/መ/ቁጥር 212876

ጉዳዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች እና በስር 1ኛ ተከሳሽ ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ተከሳሾች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 32/1/(ሀ)(ለ) እና የጦር መሳሪያ አስተዳደር እነ ቁጥጥር አዋጅ ቁትር 1177/2012 አንቀጽ 22(3) ድንጋጌን በመተላለፍ በጋራ በመሆን በሕግ የጸና ፈቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሳሪያን በሕገ-ወጥ መንገድ ለማዘዋወር አስበው ታሕሳስ 01ቀን 2013 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 7፡30 ሰዓት በሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ገብራ ጉራቻ ከተማ ቀበሌ 01 ልዩ ስሙ ሞኔካ ሆቴል በሚባል ቦታ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-A36272 በሆነ አይሱዙ የጭነት መኪና ከጎጃም መስመር ወደ አዲስአበባ ከተማ በ1ኛ ተከሳሽ ሲሽከረከር በነበረው ላይ በሕገወጥ ብዛቱ ሰባት የሆነ ብሬን የጦር መሳሪያ የአንዱ ግምት ብር 37620 በአጠቃላይ ብር 26,3340.00 የሚያወጣ ጭነው በመጓዝ ላይ እያሉ መኪናው ራዲያተሩ ውሃ ስላሞቀ ውሃ ለመጨመር ሲቆም ውስጡ ሲታይ ሁለት ብሬን የጦር መሳሪያ በመኪናው ጋቢና ውስጥ በማዳበሪያ ጠቅልሎ መደበቁን ሰዎች ሲያዩት አመልካች የጫነው ሽቶ ነው ገንዘብ እሰጣችኋለሁ ልቀቁን ብላ እነሱ እምቢ ሲሉ ሁለት ብሬን እዚያው ትተው መኪናውን አስነስተው ሲሮጡ የፀጥታ አካል ባደረገው ክትትል ደገም ወረዳ እና ጅሩ ቢሻን ዲሞ ቀበሌ ልዩ ስሙ ወራቢ በሚባል ቦታ መኪናው ከእነተከሳሾች ተይዘው ወደ ፖሊስ ጽ/ቤት ተወስደው መኪናው ሲፈተሸ ሌላ 5 ብሬን እጅ ከፍንጅ በመያዙ የጦር መሣሪያ ማዘዋወር ወንጀል ፈፅማለች  የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ …………

Print
5088

Documents to download

  • 212876(.pdf, 836.3 KB) - 615 download(s)