Thursday, March 27, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና አቶ ካሳ ጉንቲራ የሰ.መ.ቁ.246938 የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት የክስ አቤቱታ፡ አመልካች በቁሊቶ ከተማ ዞቤቻሜ ክ/ከተማ ዉስጥ ለኢንቨስትመንት የሰጠኝ እና ካርታ ያገኘሁበትን መጠኑ 4730.5 ካ.ሜ የሆነዉን ይዞታ ተገቢዉን ካሳ ሳይከፍለኝ እ ምትክ ቦታ ሳይሰጠኝ ሊያስለቅቀኝ እያስገደደኛ ስለሆነ ቀደም ሲል ያልተገመቱ ንብረቶች በባለሙያ ተገምቶ ወቅቱን ባገናዘብ ዋጋ እና ምትክ ቦት እንዲሰጠኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ የአሁን አመልካች በዚህ ክስ ላይ መልስ እንዲሰጥ መጥሪያ ተለጥፎ ሊቀርብ ባለመቻሉ ጉዳዩ በሌለበት እንዲታይ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ በመስጠት፣ የተጠሪን ክስና ማስረጃ በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪ ለክርክር ምክንያት የሆነዉ ይዞታ ለኢንቨስትመንት የተሰጠዉ መሆኑ በቀረበዉ ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ፣ ተጠሪ ዘርዝሮ ያቀረባቸዉ ንብረቶች ተመጣጣኝ ካሳ እንዳልተከፈለዉ በማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ፣ እነዚህ ንብረቶች በባለሙያ በወቅቱ ዋጋ ተገምቶ ካሳ እንዲከፈለዉ እና ለተወሰነዉ ኢንቨስትመንት ቦታዉ ተመጣጣኝ ምትክ ቦታ እንዲሰጠዉ በማለት ፍ/ቤቱ ወስኗል፡፡ መልካም ንባብ… Print 367 Documents to download 246938(.pdf, 860.35 KB) - 124 download(s)