Tuesday, June 1, 2021 / Categories: Judgement, 2013, Cassation የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ከ ኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሀረሪ ሕዝብ ክልል መንግሥት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ከክልሉ ውጭ የሚኖር የሐረሪ ሕዝብ ከዚህ ቀደም እንደነበሩት አምስት አገራዊ ምርጫዎች በ6ኛው አገራዊ ምርጫም ከክልሉ ዉጭ ያሉ የብሔረሰቡ አባላት ለሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ሊመርጡ ይገባል በሚል ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን ማስተናገድ እንደማይቻል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ የሀረሪ ሕዝብ ክልል መንግሥት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ምርጫ ቦርዱ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም የይግባኝ ቅሬታውን ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቧል፡፡ የፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 205809 ሚያዚያ 19 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ የሰጠውን ውሳኔ ውድቅ በማድረግ ቦርዱ ከክልሉ ውጪ ያሉ ሐረሪዎች የመምረጥ መብትን አስቀድሞ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ተግባራዊ እንዲያደርግ ወስኗል፡፡ በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኘው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይግባኝ ችሎቱ የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ጉዳዩን ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበ ቢሆንም የሰበር አቤቱታውን የተመለከተው የፍርድ ቤቱ ሰበር ችሎት በሰ/መ/ቁ 207036 ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም ጉዳዩን በጥልቀት ከመረመረ በኋላ በሰጠው ውሳኔ የይግባኝ ሰሚ ችሎቱ የሰጠውን ወሳኔ አጽንቷል፡፡ Previous Article ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከ ኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ Next Article ወ-ሮ አበባዬ ጌቶ እና ወ-ሮ ወርቅዬ ጌቶ የሰ-መ-ቁ 187253 Print 17154 Tags: የተከላካይ ጥብቅና አገልግሎት ሰበር ችሎት በሰ/መ/ቁ 207036 Documents to download የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከ ሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ መዝገብ ቁጥር 207036(.pdf, 11.56 MB) - 1030 download(s)