Friday, July 15, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation የሶረታ መካነሔዋን መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን እና መሐመድ ሁሴን የሰ/መ/ቁጥር 213492 ክርከሩ በተጀመረው በነቀምቴ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ከሣሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሣሽ ነበሩ፡፡ አመልካች ጥር 4ቀን 2013 ዓ/ም በተፃፈ ክሷ በነቀምቴ ከተማ 25 ሄክታር ስፋት ያለው መሬትን ከ1972ዓ/ም ጀምሮ ይዛ እየተጠቀመች መሆኑን ተጠሪው በምስራቅ ስለሚዋስናት በ2010ዓ/ም ከይዞታዋ ላይ 1600 ካሬ ሜትሩን በመውሰድ ስለያዘባት ክስ አቅርባ ክሣችሁን አላረጋጣችሁም ተብሎ መዝገቡ መዘጋቱ ለራሱ እንደተወሰነለት በማስመሰል እንደገና ህዳር 20 ቀን 2013ዓ/ም 500 ካሬ ሜትር ጨምሮ በጥቅሉ 2100 ካሬ ሜትር መሬት በመያዝ በመሬቱ ላይ የነበረውን 200 ባርዛፍ ቆርጦ የወሰደባት መሆኑን በመዘርዘር ያጠረውን አጥር አፍርሶ ይዞታውን እንዲለቅላት የንብረት ግምት እንድታቀርብ መብቷ እንዲጠበቅላት ጠይቃለች፡፡መልካም ንባብ…… Print 12500 Documents to download 213492(.pdf, 836.38 KB) - 936 download(s)