/ Categories: CASSATION, Cassation

የቻይና ኮሚኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒየ እና እነ ወ/ሮ ለምለም ተሾመ (4ሰዎች)ሰ/መ/ቁ 256185

ጉዳዩ የጉዳት ካሳን የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ በተጀመረው የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ፣2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ እንደዚሁም አመልካች፣3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ጣ/ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡1ኛ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት የክስ ይዘት በአጭሩ 2ኛ ተጠሪ በራያ ቆቦ ወረዳ 01 ቀበሌ የሚገኘውን ይዞታዬን የባቡር መንገድ ድልድይ ሲሰራ መሬቴንሙሉ በሙሉ በጎርፍ በማስወሰድ ዘላቂ ጉዳት ያደረሰብኝ በመሆኑ የ1ዓመት አላባ 28‚800 ሲሆን የ10 ዓመት አላባ 288‚000 (ሁለት መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺህ) እንዲሁም መሬት ሙሉ በሙሉ የተጎዳ በመሆኑ ምትክ መሬት እንዲሰጠኝ አልያም ብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሺህ) ካሳ እንዲከፈለኝ የሚል ነው፡፡2ኛ ተጠሪም በሰጡት መልስ በንዑስ ተቋራጭነት የዋናው ስራ ተቋራጭ ከሆነው አመልካች በተሰጠን ዲዛይን መሠረት የሠራን ሲሆን ከተሰጠን ዲዛይን ውጭ የሠራነው ነገር የሌለ በመሆኑ አመልካች ወደ ክርክሩ እንዲገባልን ሚል ነው፡፡አመልካችም ወደ ክርክሩ እንዲገባ ተደርጎ ክሱ በይርጋ የሚቋረጥ ነው በሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬ ነገር ላይም በሰጡት መልስ የሠራነውን የባቡር ድልድይ ዲዛይን 3ኛ ተጠሪ ምንም አይነት ችግር የሌለበት መሆኑን አረጋግጦ ያፀደቀው ነው፣ጉድለት ካለበትም ሰሪው ተከሳሽ ስለሆነ ኃላፊነት ያለባቸው ተከሳሽ እና 3ኛ ተጠሪ ናቸው፣ጉዳቱ የደረሰው ተፈጥሮአዊ በሆነ ጎርፍ ምክንያት ነው እንጂ ድልድዩ በመሰራቱ ምክንያት አይደለም፡፡መሬቱ ካሳ የተከፈለበት ነው በሚል 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ወደ ክርክሩ እንዲገቡ ትዕዛዝ እንዲሰጥ የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡3ኛ ተጠሪም ይርጋን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት በማንሳት የተከራከሩ ሲሆን በፍሬ ነገር ክርክራቸውም መሬቱ ካሳ የተከፈለበት ነው፣ ከተከሳሽ ጋር ምንም አይነት ውል የለንም፣ውላችን ከአመልካች ጋር ሲሆን በውላችን አግባብ ማንኛውንም ኃላፊነት የሚወስደው ራሱ ተቋራጩ ነው ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ፍ/ቤቱም በዲዛይኑ ውስጥ የፍሳሽ ማስወገጃው ከድልድዩ የሚወጣውን ጎርፍ ተከትሎ ቋሚ ስራ ያልተሰራለት ስለመሆኑ በቀረቡት ምስክሮች ተረጋግጧል፣የፍሳሽ ማስወገጃ በዲዛይን ውስጥ ስራውም ተካቶ አልተሰራም፣የባቡር መስመር ስራውን ዲዛይን የሚሰራው አመልካች ሲሆን የሚያፀድቀው ደግሞ 3ኛ ተጠሪ በመሆኑ ያልተነጣጠለ ኃላፊነት አለባቸው፣ለከሳሽ የሚከፈለውን የጉዳት ካሳ በተመለከተ የ2008 እና የ2009 አላባ በ2 ዓመት ይርጋ የተቋረጠ ሲሆን የ2010 ለ2011 እና የ2011 ለ2012 ያለው የሰሜን ወሎ ዞን ገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም በላከው ውጤት አግባብ እና የቀሪው የ10 ዓመት ዘላቂ የመፈናቀል ካሳ የአመቱ በ10 ዓመት ተባዝቶ በመጣው ውጤት ሊወሰን ይገባል በማለት በአጠቃላይ 375‚060 ባልተነጣጠለ ኃላፊነት እንዲከፍሉ በሚል ወስኗል፡፡መልካም ንባብ…

Print
4440

Documents to download

  • 256185(.pdf, 1.07 MB) - 625 download(s)