Tuesday, February 22, 2022 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ገቢዎች ቢሮ እና አቶ አዕምሮ ዘሪሁን የሰ/መ/ቁ.210727 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው ተጠሪ በባሕር ዳር ከተማ ገቢዎች መምሪያ የታክስ ኦዲትና የሕግ ማስከበር የሥራ ሂደት አስተባባሪነት ከነበሩበት ኃላፊነት ተነስተው ከደረጃ 9 ወደ ደረጀ 8 ዝቅ ብለው በሽያጭ መመዝገቢያ ኤክስፐርት ሆነው እንዲሰሩ በመመደባቸው ቅሬታ አቅርበው ተቀባይት በማጣቱ ለአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የአስተዳደር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ጥፋት ሳይኖረብኝና የዲሲፕሊን ክስ ሳይቀርበብኝ ከሥራ መደቡ መነሳቴ ሆነ ከደረጃና ደመወዝ ዝቅ መደረጌ አግባብ አይደለም የሚል ሲሆን አመልካች ባቀረበው መልስ በደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 9(4) መሠረት ማንኛውም የሥራ ሂደት አስተባባሪ በአሳማኝ ምክንያት ከኃላፊነት ሲነሳ ከያዘው መደብ ዝቅ ብሎ እንደሚመደብ ስለሚገልጽ በዚህ አግባብ የተከናወነ ነው ብሏል፡፡………… Previous Article ፌደራል ስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና ወ/ሮ ፍሬህይወት ተረፈ የሰ/መ/ቁ፡- 209987 Next Article የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ-ክርስቲያን ኮሚሽን እና አቶ መስፍን አዱኛ የሰ/መ/ቁ. 211260 Print 13741 Documents to download 210727(.pdf, 831.51 KB) - 1113 download(s)