/ Categories: CASSATION, Cassation

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ዐቃቤ ህግ ዓ/ህግ እና ደሳለኝ ቸኮል የሰ/መ/ቁ.201365

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ ያለደረሰኝ እና የጭያሽ መመዝገቢያ ማሽን ግብይት መፈፀም ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው አመልካች በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪን ጨምሮ በሁለት ሰዎች ላይ ባቀረበው ክስ ነው፡፡ በቀረበው ክስ ላይ ተጠሪ ሁለተኛ ተከሳሽ ነበር፡፡ የቀረበው ክስ ጭብጥም ተከሳሾቹ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120(1) እና 128  ድንጋጌን በመተላለፍ የስር 1ኛ ተከሳሽ የድርጅቱ ባለቤት ሆኖ የአሁን ተጠሪ ደግሞ በድርጅቱ ውስጥ የመስተንግዶ ሰራተኛ ሆኖ እየሰራ እያለ ታህሳስ 16/2012 ዓ.ም ከቀኑ 6፡50 ሰዓት አካባቢ ሁለቱ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች እያንዳንዳቸው ለተጠቀሙት ሁለት ሁለት ቢራ ደረሰኝ ሳይሰጣቸው የአሁን ተጠሪ ሂሳብ የተቀበላቸው በመሆኑ ያለደረሰኝ ግብይት ፈፅመዋል፤ በዚህም ውስጥም የአሁን ተጠሪ አስተናጋጅ ሆኖ ዳረሰኝ ሳይሰጥ ሂሳብ በመቀበል ወንጀሉ እንዲፈፀም የስር 1ኛ ተከሳሽን ረድቷል የሚል ነው፡፡……… 

Print
11885

Documents to download

  • 201365(.pdf, 806.47 KB) - 864 download(s)