Tuesday, May 27, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት እና እነ(8) ሰዎች የአቶ አበበ ተመስገን ወራሾች የሰ/መ/ቁጥር---251591 የክሱ ይዘት፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 1963 የቦታ ስፋቱ 455 ካ.ሜትር የሆነ ይዞታ በ1976 ዓ.ም ከመንግስት በምሪት አግኘተዉ የግንባታ ፍቃድ በማዉጣት ቤት ሰርተዉ የካርታ ቁጥር 22091 የሆነ ካርታ ሰኔ 29 ቀን 1976 ዓ.ም ተሰጥቷዋል፡፡ ይሁን እንጂ አመልካች የቀድሞ ካርታዉን በአዲስ ለዉጦ ወይም ቀይሮ እንዲሰጣቸዉ ቢጠይቁም በተጠሪ ይዞታ ዉስጥ በGIS እና CIS የመረጃ ቋት ላይ የሚታይ ንብረትነቱ የመንግስት የሆነ የቀበሌ ቤት የቤት ቁጥር 346 ያለ በመሆኑ ተጠሪ የቀድሞ ካርታ ተመላሽ በማድረግ በተነጻጻሪ እንደሚሠራላቸዉ ያሳወቃቸዉ ቢሆንም በይዞታቸዉ ዉስጥ ምንም ዓይነት የቀበሌ ቤት በሌለበት በንጽጽር ካርታ የሚሠራበት የሕግ አግባብ ባለመኖሩ አመልካች በሕግ ተገዶ የቀድመዉን ካርታ በአዲስ ለዉጦ እንዲሰጣቸዉ እንዲወሰን የሚጠይቅ ነዉ፡፡መልካም ንባብ… Print 1840 Documents to download 251591(.pdf, 853.37 KB) - 236 download(s)