Friday, December 31, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, Cassation የአቶ ተመስገን ተሻገር እና አቶ ሞላ ታረቀኝ ሰ/መ/ቁ፡-207003 የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 267605 ሚያዚያ 15 ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ተበሎ እንዲታረምለት አመልካች ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች አንደኛ ተከሣሽ በዚህ ሰበር ክርክር ያልተጠሩት ወ/ሮ ፅጌ ወ/ጊዮርጊስ ሁለተኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ጥር 23 ቀን 2011ዓ/ም ፅፈው ባቀረቡት ክስ በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የቤት ቁጥር አደስ ተበሎ የሚታወቀው ቤትና ይዞታቸውን አመልካች በሰሜን አቅጣጫ 60 ሣ.ሜትር ሁለተኛ ተከሣሽ የነበሩት በደቡብ አቅጣጫ 30 ሣ.ሜትር ገፍተው አጥረው የያዘቡባቸው ከመሆናቸውም በላይ የአጥርና የፍሣሽ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ለመስራት የግንበታ ፈቃድ ለማውጣት የመጣው ባለሙያን ይዞታውን አላስለካም ያሉ መሆኑን በመዘርዘር እያንዳንዳቸው ገፍተው የያዙትን ይዞታ እንዲለቁላቸው እንዲወሰንባቸው ጠይቀው አመልካች ይዞታቸውን ከ1983ዓ/ም ጀምረው አጥረው ይዘው ከሚገለገሉ በስተቀር የተጠሪን ይዞታ አለማጠራቸውን ተከራክረዋል፡፡……………… Previous Article የየካ ክ/ከተማ ዐቃቤ ህግ ፅ/ቤት እና እነአቶ ብሩክ ወንድሙሰ/መ/ቁ፡-204866 Next Article የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አስ/ፅ/ቤት እና አቶ ሰለሞን ወዳጆ የሰ/መ/ቁ 208603 Print 16597 Documents to download 207003(.pdf, 727.64 KB) - 1373 download(s)