Monday, February 21, 2022 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation የአቶ አባይ ይርጋ እና የአሶሳ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማት ማኔጅመንት መምሪያ ሰ/መ/ቁ. 205862 ይህ ጉዳይ የተጀመረው በአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ በአሶሳ ከተማ የሚገኘውንና እና የይዞታ መለያ ቁጥሩ 72/30/19 የሆነውን ሱቅ ወ/ሮ ትርንጎ በላይ እና አቶ በላይ አበበ ከተባሉ ግለሰቦች ላይ በውል ገዝቼ ውሉ ፀድቆ ስመ-ሀብቱ ወደ እኔ ዞሮ ቁጥሩ 355/164 የሆነ የምስክር ወረቀት ተሰጥቶኝ ለ10 ዓመታት ያክል ስሰራበት ቆይቻለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ወ/ሮ ማሪቱ መንጌ የተባለች ግለሰብ በ2008 ዓ.ም በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይዞታ ይገባኛል ክርክር አቅርባ ጉዳዩን እንዲያጣራ የታዘዘው ተጠሪ ለፍርድ ቤቱ በላከው ማስረጃ አመልካች 15.18 ካ.ሜ ይዞታ እንዳለፍኩኝ ለአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመግለጽ በህጋዊ መንገድ ያገኘሁትን ይዞታ በፍርድ አሳጥቶኝ ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ የዳረገኝ በመሆኑ ለደረሰብኝ ጉዳት ብር 3,000,000.00 ካሳ እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቀዉን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡ክሱ እንደሚከተለው ቀርቧል……………. Previous Article ፍቅር አብራክ የእናቶችና የሕፃናት ስፔሻላይዝድ የሕክምና ማዕከል እና ዶ/ር ልንገርህ ተፈራ የሰ/መ/ቁ፡-204829 Next Article እና አቶ ሰይድ እንድሪስ እና እና የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ፡-205889 Print 9709 Documents to download 205862(.pdf, 828.76 KB) - 727 download(s)