/ Categories: CASSATION, Cassation

የአቶ ጂወይድ ሰይድ ሳሊም እና አቶ አብዱልዋሲ አህመድ ኢብራሂም(2ሰዎች) ሰ/መ/ቁ. 253517

  • ጉዳይ የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረቡትን ክስ መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡ አመልካች ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት ክስ ይዘትም በአጭሩ ታህሳስ 10 ቀን 2008 ዓ.ም በተደረገ የሊዝ ዉል መሠረት የፕላስቲክ ፋብሪካ እና የአስተዳደር ሕንፃዎችን በአጠቃላይ በ10,000,000.00 ብር የሚገመት ግንባታ አጠናቅቄ የፕላስቲክ ባግ ማምረቻ ማሽኖችን ወደ አገር ለማስገባት ስሞክር መንግስት በሚከተለዉ አረንጓዴ ፖሊሲ ልማት ምክንያት በመከልከሌ ህንፃዉን ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ሳከራየሁ ቆይቻለሁ፤ በዚህም መሠረት ለ1ኛ ተጠሪ ከነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም በወር 20,000.00 ኪራይ እየከፈሉ ሲሰሩበት ቆይተዋል፡፡ ይሁንና 2ኛ ተጠሪ ከመመሪያ ዉጪ ፋብሪካዉን አልከፍትም በሚል ያለማስጠንቀቂያ ካርታዬን በመሰረዝ ያለምንም ጨረታ ለ1ኛ ተጠሪ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የሰጠዉ በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ ከመስከረም 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያለዉን የኪራይ ገንዘብ እንዲከፍሉ እና ይዞታዉን እንዲያስረክቡኝ እንዲሁም ካርታዉ እንዲመክን ወይም ይህ ቢታለፍ የህንፃዉ ግምት በባለሙያ ተገምቶ የሚመጣዉን ብር 10,000,000.00 እንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ፡፡  ይህ ጉዳይ የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረቡትን ክስ መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡ አመልካች ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት ክስ ይዘትም በአጭሩ ታህሳስ 10 ቀን 2008 ዓ.ም በተደረገ የሊዝ ዉል መሠረት የፕላስቲክ ፋብሪካ እና የአስተዳደር ሕንፃዎችን በአጠቃላይ በ10,000,000.00 ብር የሚገመት ግንባታ አጠናቅቄ የፕላስቲክ ባግ ማምረቻ ማሽኖችን ወደ አገር ለማስገባት ስሞክር መንግስት በሚከተለዉ አረንጓዴ ፖሊሲ ልማት ምክንያት በመከልከሌ ህንፃዉን ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ሳከራየሁ ቆይቻለሁ፤ በዚህም መሠረት ለ1ኛ ተጠሪ ከነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም በወር 20,000.00 ኪራይ እየከፈሉ ሲሰሩበት ቆይተዋል፡፡ ይሁንና 2ኛ ተጠሪ ከመመሪያ ዉጪ ፋብሪካዉን አልከፍትም በሚል ያለማስጠንቀቂያ ካርታዬን በመሰረዝ ያለምንም ጨረታ ለ1ኛ ተጠሪ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የሰጠዉ በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ ከመስከረም 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያለዉን የኪራይ ገንዘብ እንዲከፍሉ እና ይዞታዉን እንዲያስረክቡኝ እንዲሁም ካርታዉ እንዲመክን ወይም ይህ ቢታለፍ የህንፃዉ ግምት በባለሙያ ተገምቶ የሚመጣዉን ብር 10,000,000.00 እንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ፡፡መልካም ንባብ…
Print
2670

Documents to download

  • 253517(.pdf, 866.13 KB) - 303 download(s)